Saturday, 28 February 2015

Dejazmach Balcha Safo (ባልቻ ሳፎ) a.k.a Dejazmatch Balcha Abanefso;

Dejazmach Balcha Safo (ባልቻ ሳፎ) a.k.a Dejazmatch Balcha Abanefso;
An Ethiopian hero at the Battle of Adwa, 1896 Dejazmatch Balcha was known by his horse name of "Aba Nefso". Taken captive in battle as a boy, the young Oromo, was raised at the Palace of Menelik II, and regarded the Emperor as his father. He was devotedly loyal to Menelik, and served him as a regional governor in various southern provinces including Sidama and Harrar as well as one of his leading military commanders. He was a hero of the battle of Adwa in 1896.
From 1898 to 1908, Balcha was Shum of Sidamo province. After the death of Dejazmach Yilma Makonnen in 1907, he became the Shum of Harar from 1910 to 1914. From 1917 to 1928, he again served as Shum of Sidamo.
After fierce disagreements, Tafari would force Dejazmach Balcha into retirement, albeit an honourable one, in 1928, from which he would emerge in 1935 to fight the Fascist invaders, by whom he was killed in 1936.
Many respect to the hero of the 1896 and 1935 Italian agressions.

Friday, 27 February 2015

Adwa Adwa Adwa


‪#‎EthiopiaTheVictoryofAdwa‬
የአድዋ ድል ዋጋውን ለማወቅ በቀኝ ግዛት የተገዙና ማንነታቸውን ያጡ ሕዝቦችን መመልከት ብቻ በቂ ነው። የአስተሳሰብ፣ የማንነት፣ የባሕል፣ የሥነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ ሆነው ወይ ከራሳቸው ወይ ቀኝ ከገዙአቸው ነጮች ሳይሆኑ መሀል ላይ ሆነው የሚዳክሩትን ተመልከት። የተወሰኑትም የራሳቸውን ማንነት ሙሉ ለሙሉ አጥተው ቅኝ የገዙአቸውን ሀገሮች ይመስላሉ። በርካታ አፍሪካውያን፣ ላቲን አሜሪካና ኤሽያውያን የዚህ ሰለባ ናቸው። እኛ ጋር በራሳቸው ላይ ችግር እያመጡ ያሉት አሁን "ሰለጠንኩኝ" በሚል የተሳሳተ አመለካከት ወይም ከዘመኑ ጋር በተፈጠሩት የሚዲያ ተጽዕኖዎች የተነሳ ምዕራባውያንን ለመምሰል እየጣሩ ያሉ ሰዎች ናቸው።

Thursday, 26 February 2015

ዝክረ ዓድዋ ፬

We are gratefull to our forfathers!! Long live adwa!!!

ዝክረ ዓድዋ ፬ (የዓድዋው ሰማዕት! የአምባላጌው ጀግና!! የጦር አበጋዙ ፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራ)

የንጉሰ ነገስቱ የመሀል ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ገበየሁ ከጣልያኖች ጋር በተደረገው በሁሉም ጦርነት የተመሰከረላቸው ጀግና ነበሩ። የአምባላጌውን ምሽግ በመስበር በጣልያን ላይ የመጀመሪያውን የድል ደወል ያሰሙት እና ዋናው የድሉ ባለቤት እርሳቸው ነበሩ። በዚህም ምክንያት በወቅቱ የፈረንሳይ ጋዜጦች “የአምባላጌው የኢትዮጵያ ጀግና” በማለት እንዳወደሷቸው ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ ፅፈዋል። የመቀሌውንም ጦርነት በደንብ ተካፍለው በጀግንነት ሲዋጉ እጃቸውን የቆሰሉ ሲሆን ከጦርነቱ በፊትም ራስ መኮነን የዕርቅ ነገር በሚነጋገሩበት ጊዜ ገበየሁ እየተዋጉ ስለ አስቸገሩ እንደ አምባላጌው እንዳይዋጉ አስረዋቸው ሳለ በኋላ ግን ላይዋጉ አስምለው አስለቀቋቸው።
በኢትዮጵያም ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከሁሉም የላቀው የአድዋ ጦርነት የተጀመረው በየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ከማለዳው ላይ ነበር። ውጊያው ከጧቱ 11፡30 ላይ በአራት ጀኔራሎች የሚመራው የጠላት ጦር በፊታውራሪ ገበየሁ፣ በዋግሹም ጓንጉል፣ በራስ ሚካዔል እና በራሥ መንገሻ ጦር ላይ በሰነዘረው ጥቃት ተከፈተ። ፊታውራሪ ገበየሁ በዚህ ጦርነት ፊት ለፊት የገጠሙት በእንዳ ኪዳነ ምህረት በኩል የመጣውን እና በጀኔራል አልቤርቶኒ የሚመራውን የጠላት ጦር ነበረ።
በጦርነቱ ፊታውራሪ ገበየሁ ከሠራዊታቸው በመለየት ጎራዴያቸውን መዘው በዋናው የትግል አውድማ፣ በተፋፋመ እና የቀለጠ እሳት ውጊያ ላይ ተወርውረው ገቡ። ዘለው እንደገቡም ከጀግናው ጓደኛቸው ከቀኝ አዝማች ታፈሠ ጋር እየፎከሩ የጠላትን አንገት በጎራዴ ሲቆርጡ እና ሲገነድሱት ቆይተው ከርቀት በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ወደቁ። የገበየሁ መሞት ለጣልያን ጦር የድል በርን የከፈተ ስለመሰለው ጀኔራል አልቤርቶኒ ደስ ብሎት “ወደ ፊት! ወደ ፊት!” የሚል መልዕክት በየግንባሩ ያስተላልፍ ነበር። ከዚህ የምንረዳው ጀኔራል አልቤርቶኒ ፊታውራሪ ገበየሁ ማን እንደሆኑ እና ጀግንነታቸውን ያውቅ ነበር ማለት ነው። ገበየሁ ከመሞታቸው በፊትም እንዲህ ተገጥሞላቸው ነበር
የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው፥
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፥
ሥለ ገበየሁ አሟሟት በመማረኩ ምክንያት አዲስ አበባ የመጣው ዠዋቫኒ ቴዶኒ የሚባለው የጠላት የጦር መኮነን በፃፈው ማስታወሻ ላይ እንደዚህ ይላል “ . . . . . በቢያንኪኒና በማዘቶ በሚመሩት መድፎች እየተመቱ ኢትዮጵያኑ ወደኋላ ሲያፈገፍጉ አይቶ ‘ፈሪ ሁሉ እንዴት ታፈገፍጋላችሁ የአምባላጌው ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ እንዴት እንደምሞት ለንጉሱ ሄዳችሁ ንገሩ’ ብሎ እየጮኸ እንደ አንበሳ ተወርውሮ በሚዘንበው የመድፍ ጥይት መካከል ገባ። እርሱን ሲያይ ሁሉም እየሮጠ ተከትሎት ገባና ከመድፈኞቹ ጋር ተጨፋጭፎ እና ገድሎ መድፈኞቹን ማረከ። በዚያን ጊዜ በመትረየሥ ተመትቶ ወደቀ። የገበየሁ ሬሳ ከወደቀበት ቦታ የኛወቹም ጀግኖች ሬሳ አብሮ በመውደቅ የሱን ሬሳ አከበረው።”
በማለት ይቀጥልና ምርኮኛ በመሆን ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በንጉሰ ነገስቱ ሰፈር ሳለ በአይኑ እንዳየው ሥለ ፊታውራሪ ገበየሁ ሕዝቡ በሙሉ ያለቅስ እንደነበረ ከዕለታት አንድ ቀን ደግሞ ከሞት የተረፈው ሁሉም ተዋጊ በየአለቃው በየአለቃው ተሰልፎ ተሰልፎ በንጉሠ ነገስቱ ፊት ሲያልፍ የፊታውራሪ ገበየሁ ወጣት ልጅ የአባቱን የተጫነ በቅሎ ይዞ ሲያልፍ አፄ ምኒልክ አይተውት ስቅስቅ ብለው ማልቀሳቸውን ያረጋግጣል።
ድል መሰዋዕትነትን ይጠይቃል በዚሁ ጦርነት እነ ደጅ አዝማች ጫጫን፣ ቀኝ አዝማች ታፈሰን፣ ፊታውራሪ ዳምጠውን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ከፍተኛ መኮንኖች እና አዝማቾች እንዲሁም ብዙ ተራ ተዋጊወች ወድቀዋል። በነዚህ ጀግኖች ሞት መላው ሠራዊቱ ነበረ ያዘነው ። ይህንኑ የሀዘን ስሜት በግጥም ተገልጧል።
ያ ጎራው ገበየሁ ምን አሉ ምን አሉ፥
ያ ትንታግ ታፈሰ ምን አሉ ምን አሉ፥
እነ ደጃች ጫጫ ምን አሉ ምን አሉ፥
ተማምለው ነበር ከጦሩ ሊገቡ፥
አገሩን አቅንተው አድዋ ላይ ቀሩ፥
ሌላ ባለ ቅኔ ደግሞ እንዲህ ብሏል።
አዝማቹ ገበየሁ ነጭን ሲጋግር፥
ታፈሰ እያረደ ስጋውን ሲመትር፥
መትረው ጋግረው ሄዱ ሳያዩ ግብር፥
የጦር አበጋዙ ፊታውራሪ ገበየሁ የአድዋ ዕለት ወደር በሌለው ጀግንነት ለሀገራቸው ነፃነት ሕይወታቸውን በመስጠት ከፍተኛ ድል እንዲመዘገብ ያደረጉ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው። በሠሩት የጀግንነት ተግባር እስከ ዛሬ ስማቸው ሥለ አድዋ በተነሳ ቁጥር ቀድሞ ይጠራል። ይልቁንም ጠላት የአድዋን ታሪክ በፃፈው መፅሀፍ ጀግንነታቸውን እና አይበገሬነታቸውን በሚገባ ይተርከዋል። ሻቃ ገበየሁ የሰናድር ያዥዎች ሹም እንደነበሩ እና በውስጣቸው የሚያዙት ጦር ቁጥሩ 3000 እንደነበረ በጣልያኖች መዝገብ ተፅፎ ይገኛል። ሲያስተዳድሩት የነበረው ግዛት አንድ ጊዜ አሣግርትን ሌላ ጊዜ ደግሞ የጉራጌን አውራጃ ነው።
የገበየሁን የፊታውራሪነት ማዕረግ መነሻ ተደርጎ ከዚያ በኋላ የጦር መሪ ሆኖ የሚሾመው ሰው ምንም ማዕረጉ ከፍ ያለ ቢሆን ፊታውራሪ እንዲባል ተወሠነ። ከአድዋ በኋላ ንጉሰ ነገስቱ ከጦራቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ የፊታውራሪ ገበየሁን የጦር አዛዥነት ቦታ በሌላ ሰው ለመተካት ወሰኑ። ይህን ቁልፍ ስልጣን ብዙ የጦር አለቆች በተለይ እነ ሊቀ መኳስ (በኋላ ራስ) አባተ ቧ ያለው ሲመኙ ቢቆዩም ንጉሠ ነገስቱ አፄ ምኒልክ የራስ ወርቅ ጨምረው በመስጠት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባ መላን) በአዛዥነት ሾሙ።
©ብሩክ ሲሳይ (Abegaz Zė Wollo) ይቀጥላል ……..
ምንጮች፡ ሥርገወ ሐብለ ሥላሴ፣ ራይሞንድ ጆናሥ እና ተክለፃዲቅ መኩሪያ

Tuesday, 24 February 2015

ኢትዮጵያና ጂቡቲ ወዴት

 ፓለቲካ - ኢትዮጵያና ጂቡቲ ወዴት?   
ኢትዮጵያና ጂቡቲ ወዴት?ዋና ዜና
18 FEBRUARY 2015 ተጻፈ በ  

ኢትዮጵያና ጂቡቲ ወዴት?

በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያለፉ ሕፃናት ሁሉ አልፎ አልፎ በአፈ ታሪክና በተረት መካከል ላይ ያሉ አወዛጋቢ የታሪክ ትርክቶችን ይማራሉ፡፡ በመሠረቱ እነዚህ ታሪኮች ለሕፃናቱ የሚሰጡት በጥንት ዘመን እንደተከናወኑ የተረጋገጡ የታሪክ እውነታዎች ተደርገው ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ በኢትዮጵያ ዘመናዊነትን በማስተዋወቅና አገሪቱን ከቅኝ ግዛት ጥቃት በመጠበቅ የሚመሰገኑ ቢሆኑም፣ ታሪካቸው ከእነዚህ አወዛጋቢ ትርክቶች የሚካተት ነው፡፡ ስለዚህ የታሪክን እውነታ ከልብ ወለድ መለየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ አፄ ምኒሊክ ከቅኝ ገዥው የጣሊያን ወራሪ ኃይል ጋር መዋጋታቸውና በዓድዋ ጦርነት ማሸነፋቸው እውነት ነው፡፡ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን መቆርቆራቸውም እንዲሁ፡፡ 
ታዲያ የልብ ወለድ ታሪክ የቱ ነው? እንደ ልብ ወለድ ከሚቆጠሩ ሕፃናት በትምህርት ቤት ስለ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ከተማሯቸው ታሪኮች አንዱ፣ ቀድሞ የኢትዮጵያ ግዛት የሆነችውን ጂቡቲን በመስጠት ከአዲስ አበባ በምሥራቅ ኢትዮጵያ አድርጎ እስከ ጂቡቲ ወደብ የሚዘልቀውን የባቡር መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት መፈረማቸውን ያትታል፡፡ ትረካው እውነት ብሎ የሚያቀርበው አንዱ ጉዳይ፣ በወቅቱ ከነበሩት ዋነኛ የአፍሪካ ቅኝ ገዥዎች አንዷ የነበረችው ፈረንሣይ አፄ ምኒሊክ መብታቸውን ለ99 ዓመታት (ከሊዝ ስምምነት ጋር ይመሳሰላል) አሳልፈው በመስጠት፣ ለባቡር ፕሮጀክቱ ገንዘብ እንዲያገኙና ግንባታውን እንዲያከናውኑ ግፊት ማድረጓን ነው፡፡
ይሁንና ይኼንን ታሪክ እውነት እንደሆነ የሚያስቀምጥ ታሪካዊ ሰነድም ሆነ ሌላ አስተማማኝ ማስረጃ ማቅረብ እንዳልተቻለ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ አንዳንድ የታሪክ ባለሙያዎች ይህ እንዳለ አያምኑም፡፡ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት የታሪክ ባለሙያው አቶ ታምራት ኃይሌ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፒኤችዲ ጥናታቸውን እያካሄዱ ሲሆን፣ ጂቡቲ በየትኛውም ጊዜ የኢትዮጵያ ሕጋዊ  ግዛት እንደነበረች የሚያስቀምጥ ታሪካዊ ማስረጃ እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፈረንሣይን ይመሩ የነበሩት ታዋቂው ሻርል ደጎል፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሁሉንም ቅኝ ግዛቶች ነፃ የሚያደርገውን ስምምነት ካፀደቀ በኋላ፣ ጂቡቲን ከኢትዮጵያ ጋር ለመቀላቀል ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር መነጋገራቸው እንደሚታመን ጠቁመዋል፡፡
እንደ አቶ ታምራት ገለጻ፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ እስከ ጂቡቲ የሚዘልቀውን የባቡር መሠረተ ልማት ለማካሄድ ኢትዮጵያና ፈረንሣይ በጋራ የፈረንሣይ - ኢትዮጵያ  የባቡር ኩባንያን ለመመሥረትና ለፈረንሣይ ለ99 ዓመታት የመጠቀም መብት ለመስጠት የተፈረመው ስምምነት የሚያምታታ ነው፡፡ ከስምምነቱ በኋላ እ.ኤ.አ. በ1917 ሥራ የጀመረው የባቡር መስመር 784 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ነበረው፡፡ በኢትዮጵያና በጂቡቲ መካከል ላለው ግንኙንት ታሪካዊ ምልክት ነው፡፡ ከባቡር መስመሩ ባሻገር የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች ተመሳሳይ ባህል፣ ብሔር፣ ቋንቋና ደም ይጋራሉ፡፡ የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች ማኅበራዊና ባህላዊ ትስስር በየትኛውም ጊዜ ያልተለወጠ ቢሆንም፣ ይህንን ለጋራ ጥቅም ለማዋል ያለፉት መንግሥታት ያደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እ.ኤ.አ. ከ1998 እስከ 2000 ድረስ ተከስቶ የነበረው አውዳሚ ጦርነት፣ አሁን በሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት ይህን ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ጥረት እንዲያደርግ ምክንያት ሆኖታል፡፡ 
የሁለቱ አገሮች ጦርነት ኢትዮጵያ ስትጠቀምባቸው የነበሩትንና በኤርትራ የሚገኙትን የምፅዋና የአሰብ ወደቦችን እንዳትጠቀም ከልክሏታል፡፡ ይህ ክስተት የኢትዮጵያ መንግሥት ከጂቡቲ አቻው ጋር በቀጥታ በመደራደር የጂቡቲን ወደብ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ እንድትጠቀም እንድትስማማ አድርጓታል፡፡ 
‹‹ኢትዮጵያና ጂቡቲ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ልዩነት እንዳላቸው በግልጽ ካሳዩት ጥቂት ገጠመኞች ውጪ፣ ዘላቂ ተፅዕኖ ያለው ግጭት ውስጥ ገብተው አያውቁም፡፡ ይህ እውነታ ቢኖርም የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በተለያዩ ምክንያቶች በሚፈለገው መጠን ጠንካራና ጤነኛ አይደለም፤›› በማለት በኢሕአዴግ ተረቅቆ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የሆነው ሰነድ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ጠቅለል አድርጎ ይገልጸዋል፡፡  
 ጂቡቲና ኢትዮጵያ የነበራቸውን ታሪካዊና የተሳለጠ ግንኙነት ዋጋ በመስጠት የጂቡቲ ወደብ ለኢትዮጵያ ተመራጭ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ‹‹የጂቡቲ ወደብ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለኢትዮጵያ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ነው፡፡ ይኼ ደግሞ ተፈጥሯዊ ምርጫ የሚሆነው ወደቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ለአብዛኛዎቹ ክልሎች ቅርብ በመሆኑ ነው፤›› በማለትም የውጭ ጉዳይ ፖሊሲው ሰነድ ያስቀምጣል፡፡ የፖሊሲው ሰነድ ለኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ገበያ የጂቡቲ ወደብ ዘላቂና አስተማማኝ አገልግሎትን በተመጣጣኝ ክፍያ እንደሚሰጥ ያረጋግጣል፡፡ ይሁንና የወደቡን ቀጣይ አገልግሎት ለማረጋገጥ ተጨማሪ የፖሊሲ አቅጣጫ እንደሚያስፈልግ ይገልጻል፡፡ ይህ ደግሞ በዋናነት ከጂቡቲ ጋር ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲፈጠርና ሒደቱ ጂቡቲያውያኑን ተጠቃሚ አድርጎ የኢትዮጵያን ጥቅም ጂቡቲያውያኑ ጭምር እንዲጠብቁት ለማድረግ፣ ኢትዮጵያ በምትጫወተው ወሳኝ ሚና ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ያመለክታል፡፡ ፖሊሲው በተጨማሪም ይህን ለማሳካት ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በርካሽ ዋጋ የኤሌክትሪክ ኃይል ልታቀርብ እንደምትችል፣ የጂቡቲን የመጠጥ ውኃ ችግር ለመቅረፍ ኢትዮጵያ መፍትሔ ልትሆን እንደምትችልና ሌሎች መሰል ስትራቴጂዎችን ያስቀምጣል፡፡
የፖሊሲው አፈጻጸም    
ባለፉት በርካታ ዓመታት ኢትዮጵያ ፖሊሲውን ለመፈጸም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጓን ማየት ይቻላል፡፡ የቀድሞውን የባቡር መስመር የሚቀይር አዲስ የባቡር መስመር በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ 700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አዲሱ የባቡር መስመር በአራት ቢሊዮን ዶላር እየተገነባ ሲሆን፣ የቻይናው ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ ብድሩን አቅርቧል፡፡ ፕሮጀክቱ በመጪው ዓመት አጋማሽ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል፡፡ ኢትዮጵያ ሁለተኛ የባቡር መስመር ግንባታ ለማድረግ እያሰበች ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያን በአፋር በኩል በጂቡቲ እየተገነባ ከሚገኘው ታጁራ ወደብ ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡ የታጁራ ወደብ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያን የፖታሽ ማዕድን ኤክስፖርት ለማስተላለፍ ብቻ እንደሚውልም ይጠበቃል፡፡
በኢትዮጵያና በጂቡቲ ድንበር ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የሚነሳ 103 ሜትሪክ ኪዩብ ንፁህ የመጠጥ ውኃን በየቀኑ ኢትዮጵያ ለጂቡቲ ማቅረቧም ሌላው ተጠቃሽ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ለማድረግ እንደ ኬንያና ሱዳን ካሉ አገሮች ጋር ስምምነት የተፈራረመች ቢሆንም፣ ከጂቡቲ ጋር ለማገናኘትና 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ለመጀመር የፈጀባት ጊዜ ጥቂት ወራት ብቻ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያና ጂቡቲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተፈራረሙት አዲስ ስምምነት በአፋር ብሔራዊ ክልል በኩል ሌላ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ለመዘርጋት የሚያስችል ሲሆን፣ አቅርቦቱንም በእጥፍ ያሳድጋል፡፡ 
ኢትዮጵያ ከፈጠረችው ሰፊ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ትስስር ተጠቃሚ የሆነችው ጂቡቲ በበኩሏ፣ 9.8 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት የወደብና የአገልግሎት ማስፋፊያ እያደረገች ነው፡፡ ከጂቡቲ ወደብና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለሥልጣን (The Port of Djibouti and Free Zones Authority) የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እ.ኤ.አ. በ2016 ሲጠናቀቅ የታጁራ ወደብ የኢትዮጵያን የፖታሽ ማዕድን ኤክስፖርት ሙሉ በሙሉ ማስተናገድ ይችላል፡፡ ጂቡቲ ከቻይና ኩባንያ ጋር በመተባበር ሰፊ ነፃ የኢንዱስትሪ ዞን ለመገንባትም አቅዳለች፡፡ ዞኑ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የሚያቅፍ ሲሆን፣ በዋናነት የኢትዮጵያ ኢንቨስተሮች ላይ አነጣጥሯል፡፡ ኢትዮጵያ ይህን አቅሟን ካልተጠቀመችበት ጂቡቲ ከቻይናና ከአውሮፓ አገሮች ኢምፖርት ለማድረግ ትገደዳለች፡፡ 
የሁለቱ አገሮች ባለሥልጣናት በጥር ወር መጨረሻ በ21ኛው የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በጂቡቲ በመገናኘት የኢኮኖሚ ውህደቱን የሚያሳልጡ በርካታ ስምምነቶችን ፈርመዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች በትራንስፖርት፣ የጋራ ድንበር የኢንዱስትሪ ዞን ለመፍጠር፣ የጉምሩክ ቢሮዎችን አንድ ለማድረግና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ የጂቡቲ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌህ ሁለቱ አገሮች ወደ ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማምራት አንድ ዕርምጃ መሻገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ ሱፍያን አህመድ ጋር በጋራ ድንበር ኢንዱስትሪያል ዞን ለመመሥረትና ከጂቡቲ ተነስቶ በአፋር ብሔራዊ ክልል በምትገኘው አዋሽ ከተማ የሚዘልቅ የነዳጅ ማስተላለፊያ ለመዘርጋት የሚያስችሉ ስምምነቶችን በስብሰባው ወቅት ተፈራርመዋል፡፡ 
‹‹በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ የቀላል አምራች ኢንዱስትሪዎች ማዕከል የመሆን ዕቅድ አላት፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ምርቶች ለተቀረው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ ለገበያው ቅርብ መሆንና ተወዳዳሪ ወደብ ሆነን መገኘት አለብን፤›› ሲሉ ሚኒስትሩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የሚኒስትሩ አባባል በአዲስ አበባ የጂቡቲ አምባሳደር በሆኑት አምባሳደር መሐመድ ኢድሪስም ተስተጋብቷል፡፡ አምባሳደር መሐመድ እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በሥራው ላይ የነበሩ በመሆናቸው፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት መሠረታዊ ለውጥ ሲያሳይ ለመመልከት በቂ ጊዜ አግኝተዋል፡፡ ‹‹አሁን ኢኮኖሚያዊ ውህደቱን ለማጠናቀቅ እየሠራን ነው፡፡ ተጨባጭ ለማድረግ የሚኒስትሮችን ስብሰባ በየወሩ እያደረግን ነው፤›› በማለትም ግንኙነቱ በሚያበረታታ ሁኔታ እያደገ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ፖለቲካዊ ውህደት
ምንም እንኳን የሁለቱ አገሮች ኢኮኖሚያዊ ውህደት ጅማሮ ላይ ቢሆንም፣ የሁለቱን አገሮች መሪዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግን ከፍ ያለውን የፖለቲካ ውህደት አጀንዳ ከማንሳት አልተቆጠቡም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በጂቡቲ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በጂቡቲ ፓርላማ ፊት ቀርበው ንግግር አድርገው ነበር፡፡ የፓርላማው አባላትን ቀልብ ከሳቡት ጉዳዮች ዋነኛው ለፖለቲካዊ ውህደት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም መናገራቸው ነው፡፡ በየትኛውም መሥፈርት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ታሪካዊ ነበር፡፡ አንደኛው ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ያደረጉት ጉብኝት በኢትዮጵያ መሪ ደረጃ የተደረገ የመጀመርያው ጉብኝት ነው፡፡ ሁለተኛ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በራሱ ታሪካዊ የሚባል ነው፡፡
‹‹እዚህ የተገኘሁበት ዋነኛ አጀንዳ የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች ፍላጎትና ጥም ለማርካት ተጨማሪ ሥራዎች እንድንሠራ ጥሪ ለማድረግ ነው፡፡ ሕዝባችን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ትብብር በተለይም ታላቅ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ግንኙነትና ኅብረት ይፈልጋል፡፡ ማን ያውቃል ከጋራ ታሪካዊ እምነታችንና ዕጣ ፈንታችንን ለማሟላት ከምናደርገው ጥረት በመነሳት የፖለቲካ ውህደት ማሳካትም እንችል ይሆናል፤›› በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጂቡቲ ፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡ ‹‹የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያዎችና ተንታኞች ለዚህ ግንኙነት ምን ዓይነት ስም እንደሚሰጡት አላውቅም፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ ግን በእርግጠኝነት ለማሳካት እየተጠጋን ነው፡፡ ምክንያቱም የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች የሚሹት ነገር በመሆኑና ልጆቻችንንም የሚገባቸው ስለሆነ ነው፤›› በማለትም አክለዋል፡፡
በተመሳሳይ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ በበኩላቸው፣ ከሁለት ወራት በፊት ጂቡቲን ለጎበኙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ውህደትን የሕዝቦች ፍላጎት ከሆነ አገሮቹ ሊተገብሩት እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
 ‹‹ፖለቲካዊ ውህደት የማይሆንበት ምን ምክንያት አለ?›› በማለት ቀደምት የሆኑት አምባሳደር መሐመድ ኢድሪስ ይጠይቃሉ፡፡ ታሪካዊ እውነትነቱ ይረጋገጥም አይረጋገጥ በአንድ ወቅት አንድ እንደነበሩ የተነገረላቸው የሁለቱ አገሮች አንድነት ቀስ በቀስ ወደ መሆን እየተጓዘ ይመስላል፡፡ ምናልባትም አሁን ታሪክን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግም ለመጻፍ ሌላ ዕድል ተገኝቷል፡፡

Monday, 23 February 2015

ሊቢያ አሳዳሪ ያጣች ሐገር

ሊቢያ አሳዳሪ ያጣች ሐገር

የሕዝቧን መሠረታዊ ፍላጎት አሟልታ በማኖር ከአፍሪቃ አቻ ያልነበራት ሐገር ዛሬ የአሸባሪዎች፤የጎጠኞች፤ የሽፍቶች፤የስደተኛ አስተላላፊዎች፤ የዘራፊዎች መናኸሪያ ሆናለች።ከአራት ዓመት በፊት አንድ መሪ ነበራት።ዛሬ አስራ-ሰባት ሺሕ መሪዎች የሚያዙት አስራ-ሰባት ሺሕ ታጣቂ ቡድናት ይርመሰመሱባታል።
ከሜድትራኒያን ባሕር ደቡባዊ ጥግ-እስከ ሠሐራ በረሐ ወገብ የሚወርድ ሠፊ ግዛትን የምታዋስን አንድ ሐገር ነበረች።ድሆች የከበቧት፤ በረሐማ ግን ሐብታም ሐገር።ሊቢያ የሚሏት።እስከ ዛሬ አራት ዓመት ድረስ አንድ ጠንካራ መሪ፤ አንድ መንግሥት፤ አንድ ብሔራዊ ጦር ነበሯት።የዛሬ አራት ዓመት የዘመተባት የዓለም ምርጥ ጦር ከዓየርና ከባሕር ባወረደባት ቦምብ ሚሳዬል ሐብት ንብረትዋን አዉድሞ፤ ዜጎችዋን ፈጅቶ፤ መሪዋን ከነ-ሥርዓታቸዉ እጥፍቶ ዉልቅ አለባት።ዛሬ ሁለት መንግሥት፤ ሁለት ጠቅላይ ሚንስትር፤ ሁለት ምክር ቤት፤ 1700 የጦር ቡድናት ይፈነጩባታል።ሊቢያ፤ ሐብት-ዕዳ፤ ብልፅግና ጥፋት፤ ሥልታዊነት መከራ የሆነባት ሐገር።
ጥቅምት 20 2011 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ሰዉዬዉ ቆሰሉ፤ ተማረኩ፤ ወዲያዉ ተገደሉ።ለሰባት ወራት ሊቢያን ሲቀጠቅጥ ለነበረዉ ለሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ጦር አዛዦች ታላቅ ፌስታ፤ በተለይም ጦሩን ላዘመቱት ለፓሪስ-ለንደን-ለዋሽግተን-መሪዎች ከፍተኛ ድል ነበር።የሊቢያ ሕዝብም ከዋሽንግተን አዲስ ተስፋ ተንቆረቆረለት።ፕሬዝዳንት ባራክ ኦቦማ።
«ይሕ ለሊቢያ ሕዝብ የረጅም ጊዜ የሥቃይ ምዕራፍ ፍፃሜ ነዉ።ከእንግዲሕ የሐገሪቱ ሕዝቦች በአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ሊቢያ የራሳቸዉን መሳኤ ዕድል መወሰን ይችላሉ።የጋዳፊ ሥርዓት ለአራት አስርታት ሊቢያን በብረት ጡንቻ ገዝቷል።መሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች ተገፈዋል።ንፁሐን ሰላማዊ ሰዎች ታሥረዋል።ተገርፈዋል።ተገድለዋል።የሐገሪቱ ሐብት ተመዝብሯልም።ሽብር እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አገልግሏል።ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ከነበሩት አምባገነኞች አንዱ ከእንግዲሕ ተወግደዋል።ይሕ በሊቢያ ታሪክ ልዩ ሥፍራ አለዉ።የሊቢያ ሕዝብ ከቃዳፊ ሥርዓት ጋር ጨርሶ የሚቃረን ሁሉን አቀፍ፤ ሁሉን አቻችላ የምታኖር ዴሞክራሲያዊት ሊቢያን የመገንባት ሐላፊነት አለበት።»
ከቃላት ባለፍ በገቢር ምንም ያልነበረዉ የሠላም የዲሞክራሲ፤ የፍትሕ ተስፋ ከበነነ ከረመ።ዴሞክራሲዊ ሥርዓት እንገነባለን ብለዉ የፓሪስ፤ ለንደን ዋሽንግተኖችን ድጋፍ ለማግኘት ሲባትሉ የነበሩት ሙስጠፋ አብዱል ጀሊል፤መሐመድ ጅብሪል፤ አብዱል አዚዝ ጎሐግና ብጤዎቻቸዉ ሐገር ሕዝባቸዉን አመሰቃቅለዉ ከፖለቲካዉ መድረክ ከጠፉ ዓመታት ተቆጠሩ።
የነሙስጠፋ አብዱል ጀሊልን የአማፂ ቡድናት ስብስብን ደገፎ ሊቢያን የደበደበዉ የሠሜን አትላቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ጦር አላም ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን እስከ-መግደል ማስገደል ከነበረ በርግጥ ተሳክቶለታል።ኦባማ እንዳሉት ሰላም፤ ዴሞክራሲ፤ ፍትሕ ማስፈን ከነበረ ግን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ እንደሚለዉ በርግጥ ዉል ስቷል።
የሕዝቧን መሠረታዊ ፍላጎት አሟልታ በማኖር ከአፍሪቃ አቻ ያልነበራት ሐገር ዛሬ የአሸባሪዎች፤የጎጠኞች፤ የሽፍቶች፤የስደተኛ አስተላላፊዎች፤ የዘራፊዎች መናኸሪያ ሆናለች።ከአራት ዓመት በፊት አንድ መሪ ነበራት።ዛሬ አስራ-ሰባት ሺሕ መሪዎች የሚያዙት አስራ-ሰባት ሺሕ ታጣቂ ቡድናት ይርመሰመሱባታል።
እንደ አንድ ሐገር አንድ መንግሥት ነበራት።ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ ከነሥራዓታቸዉ ከተገደሉ ከ2011 ጀምሮ አምስት መሪዎችና መንግሥታት ተፈራርቀዉባታል።ዛሬም ርዕሰ-ከተማ ትሪሊፖሊ ላይ አንድ መንግሥትና አንድ ምክር ቤት አላት።ቶብሩክ ላይ ደግሞ ሌላ መንግሥትና ሌላ ምክር ቤት አላት።መንበሩን ቶብሩክ ያደረገዉና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እዉቅና ያገኘዉ መንግሥት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር መሐመድ አል ዳይሪ እንደሚያምኑት ዓለም አቀፉ ድርጅት በመንግሥታቸዉ ላይ የጣለዉ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ቢነሳ የሊቢያን ችግር ማቃለሉ አይገደዉም።
«ሊቢያ፤ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ወሳኝ እርምጃ ትሻለች።የራስዋን ብሔራዊ ጦር ሐይል መገንባት ትችል ዘንድ የተጣለባት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ሊነሳላት ይገባል።»
የዳይሪ መንግሥት ትንሺቱ የወደብ ከተማ ቶብሩክ ለመሸሸግ የተገደደዉ ሊቢያን አይደለም ርዕሠ-ከተማ ትሪፖሊን እንኳ መቆጣጠር አቅቶት ነዉ።በትሪፖሊና በቶብሩክ መካከል አንድ ሺሕ ኪሎ ሜትር ተዘርግቷል።አንድ ሺሕ ኪሎ ሜትሩን የሞሉት ደግሞ እስካፍንጫቸዉ የታጠቁ፤በጎሳ፤ በጎጥ፤ በሐይማኖታዊ አስተሳሰብ የተከፋፈሉ፤ የኮሎኔል ሙዓመር ጦር ባልደረቦች የነበሩ፤ ታጣቂዎች ናቸዉ።
የቶብሩኩ መንግሥት በተቀናቃኞቹ የሚሰነዘርበትን ጥቃት የሚከላከለዉ ደግሞ ጄኔራል ኸሊፋ ሐፍትር የሚመሩት ጦር ነዉ።ሐገር መንግሥታቸዉን ከድተዉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እስከ ኮበለሉበት ጊዜ ድረስ የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ ታማኝ የጦር መኮንን የነበሩት ሐፍትር የትሪፖሊንም፤ የቶብሩክንም መንግሥታት ፈነጋግለዉ ወታደራዊ አምባገነን አገዛዝ ለማስፈን እያደቡ ነዉ።
ለዚሕ ግባቸዉ ስኬት በሕዝብ የተመረጠ መሪ በሐይል አስወግደዉ የግብፅን የመሪነት ሥልጣን የያዙትን የጄኔራል አብዱልፈታሕ አል ሲሲን ሙሉ ደጋፍ በሲሲ በኩልም የሳዑዲ አረቢያና የአረብ ኤሚሬቶች የጦርና የገንዘብ ርዳታ ይንቆረቆርላቸዋል።
«እዚያ ሊቢያ ከሶሪያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል፤ በምዕራቡ ፖለቲካዊዉ ሥርዓት ብዙም ያልተለመደ ነገር ይታያል።እስላማዊ ቡድናት አሉ።ወንጀለኛ ሚሊሻዎች አሉ።የቀድሞ ጦር ባልደረቦች አሉ።ኸሊፋ ሐፍታር ዋነኛዉ ናቸዉ።ከግብፅ፤ ከአረብ ኤምሬቶች እና ከሳዑዲ አረቢያ ርዳታ ይደረግላቸዋል።(አላማቸዉ) ለሐያማኖት ያልወገነ ወታደራዊ አምባገነን መመሥረት ነዉ።»
ይላሉ ጀርመናዊዉ የሽብር ጉዳይ አጥኚ ጊዶ ሽታይንበርግ።የግብፅና የአረብ ኤሜሬቶች የጦር ጄቶች መንበሩን ትሪፖሊ ያደረገዉን መንግሥት የሚደግፉትን ሚሊሻዎች በተደጋጋሚ የሚደበድቡትም ሲሆን ሐፍትርን ይሕ ቢቀር ሐፍትርን የሚደግፉ ሐይላትን ትሪፖሊ ቤተ-መንግሥት ለመዶል ነዉ።
ጄኔራል አል ሲሲ ከዚሕም ሌላ ትልቅ አላማ አላቸዉ።በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን መያዛቸዉን ከሚቃወሙ በተለይም ከሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበር አባላት የሚደርስባቸዉን ወቀሳ፤ትችትና አመፅን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል።
ይሁንና የአልሲሲ እርምጃ ለሊቢያ ደፈጣ ተዋጊ ቡድናት በተለይም ለፅንፈኞቹ ሐይላት ሰበብ ምክንያት ሆኖ ሲርት ዉስጥ 21 የግብፅ ኮፕቲክ ክርስቲያኖችን እስገድዷል።ከኮብቶቹ መገደል በሕዋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊቢያ አማፂያንን የሚወጋ ጦር እንዲያዘምት የካይሮ ገዢዎች እንከመጠየቅ ደርሰዉ ነበር።
የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የጦር መሳሪ ማዕቀብ ይነሳ የሚለዉን የቶብሩክ መንግሥትንም ሆነ ዓለም ቀቀፍ ጦር ይዝመት የሚለዉን የካይሮዎችን ጥያቄ አልተቀበለዉም።ምክንያቱ ሁለት ነዉ።የመጀመሪያዉ ሊቢያ ጠንካራ መንግሥት የላትም የሚለዉ-አንድ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቀናቃኝ ሐይላትን ለማስታረቅ የጀመረዉ ጥረት ይደናቀፋል የሚለዉ-ሁለት።
የአል-ሲሲ መንግሥት ግን ሊቢያን ማስደብደቡን እንደቀጠለ ነዉ።የግብፅን ጣልቃ ገብነት ቀጠርና ቱርክ በግልፅ ሲቃወሙት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችና ሳዑዲ አረቢያ ለድብደባዉ ስኬት ሙሉ ድጋፋቸዉን እየሰጡ ነዉ።
ምዕራባዉን መንግሥታት የሊቢያ ሉዓላዊነት መደፈርም ሆነ የቅርብ ወዳጆቻቸዉ የገጠሙት የእጅ አዙር ጦርነት ብዙም ያሳሰባቸዉ አይመስልም።ሶሪያ እና ኢራቅ ዉስጥ ሰፋፊ ግዛቶችን የሚቆጣጠረዉ እስላማዊ መንግሥት የተሰኘዉ አሸባሪ ቡድን ሊቢያ ዉስጥም እየተደራጀ ነዉ መባሉ ግን በተለይም የአዉሮጳ መንግሥታትን እያሳሰበ ነዉ።
የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ እንደሚለዉ አዉሮጶች ከሊቢያ የሜድትራኒያን ባሕርን አቋርጠዉ ከሚገቡ የአረብና የአፍሪቃ ስደተኞች ጋር አሸባሪዎችም ወደ አዉሮጳ ሊሻገሩ ይችላሉ የሚል ሥጋት አድሮባቸዋል።
የአረብ ሊግ ዋና፤ ዋና አባላቱ ፤ አባሉ የሆነችዉን ሊቢያን ሲያመሰቃቅሉ ሊጉ ራሱ የሌለ ያክል ድምፁን አጥፍቷል።የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጦር ሊቢያን መዉረሩን አጥብቆ ተቃወሞ የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ከሰሐራ በረሐ በስተ-ሰሜን የምትገኝ አባሉን ለማየት በረሐዉ የጋረደዉ መስሏል።
ሊቢያ ሕዝባዊ አመፅ ከተቀሰቀሰባት-ከየካቲት 2011 ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ እስከተገደሉበት እስከ ጥቅምት 2011-በተቆጠረዉ ስምንት ወር ግድም ከአስራ-አራት ሺሕ በላይ ሕዝብ አልቆባታል።ቃዛፊ ከተገደሉበት-ሁለት መንግሥት እስከተመሠረተበት እስካለፈዉ ግንቦት ድረስ ሁለት ሺሕ ሰዎች ተገድለዋል።ከአምና ግንቦት እስካለፈዉ ጥር ድረስ አራት ሺሕ ሰዉ አልቆባታል።ዛሬም ትነዳለች።አሳዳሪ ያጣች ሐገር።

History | ያልሰመረው የቤልጅየም ኢትዮጲያን የመግዛት ውጥን


(ወልደብርሃን ስሁል)
የዛሬ መቶ ሰባ ዓመት አካባቢ አንዲት “ሚጢጢየ” አውሮፓዊት ሃገር ማንም ሳይቀድማት ኢትዮጵያን በጉልበት ይዛ ቅኝ ለመግዛት “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብላ” ቆርጣ ተሰናዳች። በቆዳ ስፋቷ አንድ ትልቅ ወረዳ እምታክል ናት። አፍሪካ ውስጥ ግን የራሷን መቶ እጥፍ የሚያክል ግዛት መቆጣጠር እሚያስችል አቅምና እብሪት ነበራት። ህልሟን ለማሳካት ፕሮጀክት ቀርፃ feasibility study አካሄደች። እቅዷና ጥናቷ ያነጣጠረውም በዘመነመሳፍንቷ ኢትዮጵያ ላይ ነበር። የቀይ ባህር አካባቢ ደከም ባለ አውሮፓዊ ሃይል እንዲያዝ ትሻ የነበረችው ታላቋ ብሪታንያም ይሁንታ ሰጠቻት፤ በወርራ ቅኝ ልትገዛን ቆርጣ ለተነሳችው ቤልጅየም!
ቤልጅየም ለኢትዮጵያ ያሰበችው ፕሮጄክት ብሎንዲል ከሚባል እብሪተኛ ሰው የጀብድ ልክፍት ጋር የተቆራኘ ነበር። ግብፅ በወርኔር ሙዚንጀር፤ ጣልያን በፔትሮ አንቶኖሊ ምን እንዳደረጉን ጠንቅቀን እናውቃለን። ከነሱ በፊት ቀድሞ ስለተሰናዳልን የብሎንዲል Humanitarian Mission ግን ብዙ አናውቅም። ነገሩ ያስገርማል እንጂ አያስቅም። “ገድለ‐ብሎንዲል” በጥቂቱ እንዲህ ነበር፦
የቤልጂግ መንግስት መጀመርያ በ1841 ከፍተኛ በጀት መድቦ ብዛት ያላቸው የስለላ ወኪሎቹን ወደ ግብጽ አሰማራ። ወኪሎቹም “ለሳይንሳዊ ጥናት እና ለሰብአዊ ተልእኮ” በሚሉ ሽፋኖች ካይሮ ላይ ከትመው ስለ ኢትዮጵያ ጥናት ጀመሩ። ማንኛውንም ዓይነት መረጃ በዝርዝር እየቀራረሙ ከሚያቀርቡት ሪፖርት የቤልጂየም ንጉስ ቀዳማዊ ሊዮፖልድ “በውስጧ ሁከት የነገሰባት ኢትዮጵያን” በቀላሉ መውረርና መቆጣጠር እንደሚችል አመነ። ለወረራም ቋመጠናም የሰላዮቹ አስተባባሪ በአካል ወደ ኢትዮጵያ ሂዶ “ሰብዓዊ ተልእኮ” የሚል ስም ያለው ጉብኝት እንዲያካሂድ አዘዘው። ዋናው ተልእኮው ግን ለወረራ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር እና ባስቸኳይ እሚተገበር የድርጊት መርሃ ግብር እንዲያዘጋጅ ነበር። ይህን ሃላፊነት የተቀበለው የሰላዮቹ አለቃም ካይሮ ተቀማጩ በግብጽ የቤልጂክ መንግስት ዋና ቆንሲላ የነበረው ብሎንዲል ነው።Map - Belgium
ብሎንዲል የፖለቲከኞቿ እርስበርስ ጥልና ፉክክር በመጠቀምና የካቶሊክ እምነት በማስፋፋት ኢትዮጵያን በቀላሉ ቅኝ ማድረግ ይቻላል ብሎ አምኗል። ይህ እምነቱም ጽኑ ስለነበር የተለየ ነገር ሰምቶና አይቶም አልለወጠውም። ብሎንዲል ገና ካይሮ እያለ አዲስ ፓትሪያርክ ሊያመጡ ወደ ግብጽ የሄዱ የኢትዮጵያ ልኡካን አግኝቶ ጉዳዩን “የቤልጅየም መንግስት ለአቢሲኒያውያን የሰብዓዊ እድገትና ስልጣኔ ካለው ተቆርቋሪነት” አንጻር አዋዝቶ እየተነተነ አጫወታቸው። እነሱም (ከመካከላቸው አንዲት ፀጉር ለብዙ ሰንጥቀው ብዙ እሚሟገቱ ነቄ ካህናት ነበሩ) አዋዝተው መለሱለት፦ ጥንት ጀምሮ የኦርቶዶክስ ክርስትና በተስፋፋባት ሃገራቸው የካቶሊክ እምነት ተቀባይነት እንደማያገኝ፣ እስላሞቹም ሆኑ ክርስቲያኖቹ ኢትዮጵያውያን ተባብረው በጋራ ሃገራቸውን ከጠላት እንደሚጠብቁ፣ የየአካባቢው መሳፍንት በአንድነት የውጭ ወራሪን እንደሚመክቱ በማሳሰብ ብዙ ምሳሌ ጠቁመው ሃሳቡ እንደማይሳካ…በትህትና ነገሩት። አጅሬ ግን ሊያምን አልፈቀደም። በመጨረሻ በ1841 ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በየመሳፍንቶቹ አካባቢዎች እየተዘዋወረ “ለሰብዓዊ ተልእኮው” የሚያመቹ ቆላና ደጋ የአቢሲንያ መሬቶችን እየማተረ ሰነበተ።
ብሎንዲል በቆይታው የትግራዩን ደጃች ውቤ፣ የበጌምድሩን ራስ አሊ እና የጎጃሙን ደጃች ጎሹ ተራ በተራ ጎበኛቸው። ሁሉም ሞቅ አድርገው ተቀብለው አስተናገዱት። ከእያንዳንዳቸው ጋር ስጦታዎች እየተለዋወጠ ስላገሩና ስላገራቸው ጠቅለል ያለ ውይይት እያካሄደ ሁኔታቸውን አጠና። ሁሉም እንደተለመደው ለሚወዱት ታቦት የሚሰጥ የቤተክርስቲያን ደወል፣ ለግላቸው የሚታጠቁት እሚያምር ሽጉጥ ወይም ጠመንጃ…ግፋ ካለም እነዚህን ነገሮች የሚሰራ ጎበዝ የፈረንጅ አንጠረኛ ከቤልጀም ቢመጣላቸው እንደማይጠሉ ነገሩት። በፖለቲካ ቋንቋ ሲመነዘር ከአውሮፓ ወታደራዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ ከመጠየቃቸው ውጭ ከመካከላቸው ለቤልጂየም ፍላጎት ተባባሪ ሊሆን የፈቀደ አንድም አልነበረም።
ብሎንዲል ግን ከታዘበው አጠቃላይ ሁኔታ ተነስቶ የራሱ ድምዳሜ ላይ ደረሰና በአፉ ለሚናገረው ሰብዓዊ ነገር ሳይሆን ከልቡ ለያዘው ኢሰብአው ተልእኮ የሚመቹ አጋሮች መረጠ። ደጃች ውቤ ስሜን፣ ትግራይና ባህረ ነጋሽ ባንድ ላይ ያጠቃለለ ስትራቴጂክ ግዛት ስለሚያስተዳድር፣ ግዙፍ ሰራዊት ስለሚመራ እና ከሌሎቹ ተፎካካሪዎቹ በተሻለ ንጉሰ ነገስት ለመሆን ዝግጅት ላይ ስለነበር ለአጋርነት አልታጨም። ውቤ ኢትዮጵያውያንን አሰተባብሮ ጠንካራ ሃይማኖታዊና ወታደራዊ መከላከል አካሂዶ የቤልጅየምን ህልም ሊያጨልም ይችላል ብሎ ስለፈራ የብሎንዲል አይን ራስ አሊ እና ደጃች ጎሹ ላይ አረፈ። በሱ እምነት ራስ አሊ “ከአንጀቱ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ስላልሆነ” ከግብፁ መሪ መሃመድ አሊ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችን እንዲወጋ ማድረግ እንደሚቻል እርግጠኛ ሆኗል። ደጃቸ ጎሹ ደግሞ ቀደም ብሎ ፖርቱጋላውያን የካቶሊክ እምነት በተወሰነ ደረጃ ያስፋፉበትን አካባቢ ስለሚያስተዳድርና “ከሌሎቹ የአቢሲንያ መሪዎች በተለየ የአውሮፓውያን ስልጣኔ ለመቀበል ትልቅ ፍላጎት ያለው ምሁር ሃገረ ገዢ በመሆኑ” ሚሲዮናውያንና የእደጥበብ ባለሙያዎች ቢላኩለት ኢትዮጵያ ውስጥ የካቶሊክ እምነት በማስፋፋት የቤልጅየምን ህልም ለማሳካት እንደሚጠቅም አመነ። ብሎንዴል ወደ ካይሮ ተመልሶ ይህንኑን ድምዳሜ ለቀዳማዊ ሊዮፖልድ በደብዳቤ አሳወቀ። ቀጥሎም ኢትዮጵያን በወታደራዊ ወረራ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዝርዝር እቅድ አዘጋጅቶ ረቂቅ ፕሮፖዛሉን በሴፕቴምበር 30፣ 1843 ለቤልጅየም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቀረበ።
ፕሮፖዛሉ ባጭሩ ሲቀመጥ ቤልጅየም በወረራ ኢትዮጵያን በቀላሉ ተቆጣጥራ እና የውስጥ ዓመጽ አክሽፋ በይዞታዋ ስር ማቆየት ትችላለች ይላል። ለዚህም እንደተጨባጭ የቀረቡት ማሳመኛዎች ደግሞ “ኢትዮጵያ ህዝቦቿ ተራራን መከታ ከማድረግ ውጭ ዘመናዊ ጦር መሳሪያ የማያቁ መሃይማን መሆናቸው፣ በሃገሪቱ ውስጥ የማያባራ የእርስበርስ ብጥብጥ የተለመደ ክስተት መሆኑ፣ ህዝቦቿ በሁሉም ነገር ኋላ ቀር መሆናቸው…” የሚሉ ናቸው። ከዚህ ጋር አብሮ አንድ አስገራሚ የማሳመኛ ነጥብ ተካትቷል ቀረቦ። ራሱ ብሎንዲል ቀደም ብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አሰራጨሁት ያለው የፈጠራ ትንቢት፦ “ኢትዮጵያ በፈረንጅ ትወረራለች ነጭ ንጉስም ይገዛታል፤ ህዝቦቿም እንደ ፈረንጆች በእውቀት፣ በሃብትና በጽድቅ ይንበሸበሻሉ” የሚል ራሱ ያሰራጨው የፈጠራ ትንቢት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል በማለት ቤልጅየም ወረራ ስትፈፅም ኢትዮጵያውያን “ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው” ብለው “ለነጩ ንጉስ እጃቸውን በቀላሉ ይሰጣሉ” የሚል ቂላቂል መሟገቻ ፕሮፖዛሉ ውስጥ አቅርቧል። ብሎንዲል ከፕሮፖዛሉ ጋር አብሮ ያቀረበው ረቂቅ ወታደራዊ እቅድም እጅግ መሳጭ ነው። ቤልጅየም ኢትዮጵያን ለመውረር በምታካሂደው ዘመቻ 230 መድፈኞች፣ 100 ፈረሰኞች፣ 870 እግረኛ ወታደሮች ያሉት ሰራዊት እና 1200 ድጋፍ ጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች የጉልበት ሰራተኞች ማክተት ብቻ በቂ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል። በጁን 19 ቀን 1844 የቤልጂክ መንግስት ይህንን ዝርዝር ወታደራዊ እቅድ አጽድቆ ወረራው እንዲፈጸም ወሰነ፤ ታላቋ ብሪታንያም መልካም ፈቃዷን ሰጠች።
ከዚያ በኋላ “ሚጢጢየዋ” ቤልጅየም “ታላቋ” ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት መዳፏ ስር ልታስገባ ወታደራዊ መሰናዶዋን አጣድፋ አጠናቀቀች። አውሮፓ ውስጥ የብሎንዲል “ሰብዓዊ ተልእኮ” /Humanitarian Mission/ ወዳፈጠጠ “ወታደራዊ ወረራ” /Outright Aggression/ መሆን የሚያስችለው ይፋዊ እውቅና ተሰጥቶት ብራሰልስ ውስጥ ነጋሪት ሲጎሰም ኢትዮጵያውያን ስለጉዳዩ የሚያውቁተ ሃባ ነገር አልነበረም። ሌላው ቀርቶ ብሎንዲን ለስለት የሚሰጡ የስጦታ እቃዎች ወይም እሚያምሩ ትጥቆች አልያም ጎበዝ አንጠረኛ እንዲልክላቸው “አደራ” ያሉት መሳፍንት እንኳ በእርስበርስ ፉክክርና ጦርነት ተወጥረው ስለነበር እሱ ከሄደ በኋላ የሱን ስምና ያገሩን ስም የሚያስታሱበት ጊዜ አልነበራቸውም። ባይሆን “አደራ” ያሉትን ስጦታ ወይም አንጠረኛ ቢልክላቸው ወይም ራሱ ይዞ ቢመጣ ኖሮ የጦረኛ ካባ ኣልብሰውና በቅሎ ከነ ሙሉ ሽልማቷ ጀባ ብለው ወዳገሩ ይሸኙት ነበር፤ የሱና የሃገሩም ስም በኢትዮጵያ ታሪክ ይሰፍር ነበር። እሚገርመው ግን የብሎንዲል ገድልም ኢትዮጵያ ሳይደርስ እዚያው ላይ አበቃ።
ቤልጅየም ለወረራ ቀን ቆርጣ ሽርጉድ ካለች በኋላ ፕሮጄክቷን ድንገት ተወችው። ጓቴማላ ላይ ያቀደችው ተመሳሳይ ፕሮጀክት ስለነበር እሱን ማጠናከር ይሻለኛል ብላ። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያን እንዲህ አቅልሎና አሳንሶ ያየው የብሎንዲል እቅድ “Castle in the air” (ላም አለኝ በሰማይ) ብለው የቅኝ አገዛዘ ዘመን ታሪክ ጸሃፍት ተሳልቀውበታል። መቼም የቤልጂየም ቅኝ አገዛዝ ባለስልጣናት ከጓቴማላ በኋላ ወደ አፍሪካ ሰራዊታቸውን አዝምተው ኮንጎን ወርረው መያዛቸው አልቀረም። ታዲያ ምን ሁነው ነው ከጓቴማላ በኋላ መጀመሪያው ቋምጠው ወደ ተሰናዱበት ወደ አፍሪካ ቀንድ ያልመጡት ብለን ብንጠይቅ ካልተከናወነ ታሪክ የቢሆን ኖሮ መልስ ማግኘት ይከብዳል። ከዚያ በኋላ አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ከተፈጸመው ታሪክ ተነስተን ስንገምት ግን በጠንቃቃዎቹ ቤልጂያኖች ልብ “ግብፅንና ጣልያንን ያየ ኢትዮጵያ ጋር አይሳፈጥም” የሚል ብሂል ተቀብሮ ተቀምጦ ሊሆን እንደሚችል እንጠረጥራለን።
አይበለውና እነብሎንዲል እቅዳቸውን በወቅቱ ፈጽመው አሳክተውት ቢሆንስ ኖሮ ውጤቱ ምንይሆን ነበር? በእርግጥም ኢትዮጵያ እንደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የትልቅ ትንሽ ከመሆን አልፋ ለአፍሪካውያን ሰብዓዊ መብት የሚቆረቆሩ ፈረንጆች ፕሮጄክታቸው ሲሳካ ምን አይነት ሃገርና ህዝብ እንደሚፈጥሩ ልክ እንደ ኮንጎዎች ከሰውነት ወደ እንስሳነት ወርደን ለአዓም እንመሰክር ነበር። አሁን በሃያኛው ክፍለዘመን በፈረንጅ ሃገር ስለ “ሰብዓዊ መብት” /Human Rights/ አፋቸውን ሞልተው እየተመጻደቁ የሚለፍፉ ፈረንጅና የፈረንጅ ወኪል “ተቆርቋሪዎች” ትረካዎቻቸው የ19ኛው ክፍለዘመን ሰነዶች ከተከማቹባቸው የአውሮፓ ቤተመዘክሮች ሂደው ከብሎንዲል Humanitarian Mission መሰል ፕሮፖዛሎች ገጽ በገጽ ቃላት ገልብጠው ሲጠቀሙ እናስተውላቸዋለን።
ልክ እንደብሎንዲል ከአፋቸው እሚያማልሉ ጣፋጭና ተቆርቋሪ ቃላት ይወጣሉ፤ በልባቸው የውስጥ ቁርቁሳችን ላይ ያተኩራሉ፤ አንዳንዶቹም አፍሪካውያን እርስ በርሳችንም እንድንጠፋፋ ሌት ተቀን ተግተው ይሰራሉ። ደግነቱ ተግባር ላይ ሲመጣ “ጉዳዩ ሃበሾችን አይመለከትም” የሚል የውስጥ መግባብያ ወይም ያልተጻፈ የተግባር መመርያ የሚጠቀሙ ይመስላል። “ገድለ‐ብሎንዲል” ባጭር የተቀጨው በዚህ መመርያ ይሆን?
**********  
https://www.facebook.com/abiy1702

Just Begin

Just Begin