Monday, 31 August 2015

Who Owns the Nile ?

የአባይ ጉዳይ ከምር  በጣም  ያማል !! 66% ለግብፅ - 22% ለሱዳን  ቀሪው 12% በ ኢቫፖሬሽን ይሚጠፋ !!! ኢትዮጽያ 0% !! #Abiy1702     Who owns the Nile ? Abiy1702

Who owns the Nile? It's more complicated than you think
Source: Al Jazeera and agencies

Tuesday, 4 August 2015

ወዳጅና ጠላት ያለየበት ጦርነት !!

ወዳጅና ጠላት ያለየበት ጦርነት

ምዕራባዉያን መንግሥታት ISISን በምድር የሚወጉትን የኢራቅና የሶሪያ ኩርዶችን በቀጥታ፤የቱርክ ኩርዶችን ደግሞ በተዘዋዋሪ ያስታጥቃሉ።ቱርክ ኩርዶችን ትወጋለች፤ ኩርዶችም ቱርክን።ምዕራባዉን መንግሥታት፤ቱርክና አረቦች የደማስቆ ገዢዎችን የሚወጉ አማፂያንን ይደግፋሉ።ISISም የደማስቆ ገዢዎችን ይወጋል።

ወዳጅና ጠላት ያለየበት ጦርነት

የዋሽግተን፤ ብራስልስ ጥብቅ ወዳጆ፤የሪያድ፤ ዶሐ፤አማን፤ ኤርቤል ታማኞቻቸዉን አስቀድመዉ የቴሕራን-ደማስቆ ጠላቶቻቸዉን እየወጉ፤እያስወጉ፤ ደሞ በተቃራኒዉ ከቴሕራን፤ ደማስቆ፤ ጠላቶቻቸዉና ጋር እንደ ወዳጅ ባንድ አብረዉ ISISን ይዋጋሉ።ተቃራኒዎችን እንደ ጠላት እያዋጋ፤ እንደ ወዳጅ ባሳበረዉ ጦርነት አልተካፈለችም እንዳትባል ተዋጊዎችን እየረዳች፤ ተካፍላለች እንዳይባል ጦር አላዘምትም እያለች ስታቅማማ የነበረች አንድ ያካባቢዉ ሐገር ነበረች።ቱርክ።ባለፈዉ ሳምንት ግራ-አጋቢ አቋሟን ቀይራ፤ከግራ አጋቢዉ ጦርነት በሁለት ተቃራኒ ግንባር ተሞጀረች።
የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆርጅ ዳብሊዉ ቡሽ እንደ ፊት አዉራሪ፤ የያኔዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር እንደ አጋፋሪ ኢራቅን ሲወርሩ አንድ የቱርክ ፖለቲከኛ ጠይቀዉ ነበር።« ሳዳም ሁሴን በርግጥ ከሥልጣን ይወገዳሉ፤ ግን አዲሱ ለዉሬንስ ማን ይሆን?» ብለዉ።
ጀላቢያ፤ ጥምጣም፤ ቁድራቸዉን ለብሰዉ፤ ሴሞ (ጎራዴያቸዉን) ታጥቀዉ አረብኛዉን ሲንያቆረቁሩት-አረብ፤ ሱፍ-ከራባት ለብሰዉ-በእንግሊዝኛ ነገር ሲቆላልፉ-ዲፕሎማት፤ ሸሚዝ፤ ቁምጣቸዉን አጥልቀዉ መሬት ሲቆፍሩ-የሥነ-ዕብን ተመራማዊ (አርኪዎሎጂስት)፤የጦር መለዮ፤ ማዕረጋቸዉን ሲያጠልቁ-ሻምበል ይመስሉ ነበር።ቶማስ ኤድዋርድ ለዉሬንስ።ወይም ለዉሬንስ-ዘ-አረቢያ። ሁሉንም ነበሩ።ከሁሉም በላይ ብሪታንያዉ።
ታላቅዋ ብሪታንያ መካከለኛዉ ምሥራቅን በተለይም ዛሬ እስራኤል፤ ፍልስጤም፤ ዮርዳኖስ፤ ሶሪያ፤ ሳዑዲ አረቢያ፤ ኢራቅ ተብለዉ የሚጠሩትን ሐገራት ከቱርክ እጅ ፈልቅቃ ለመዉሰድ ለነበራትን የረጅም ጊዜ ዕቅድ ገቢራዊነት አረቦችን ከጎኗ ያሰለፉ ብልጣ-ብልጥ ሰላይ፤ በሳል ዲፕሎማት፤ የጦር መኮንን ነበሩ።
በመጀመሪያዉ የዓለም ጦርነት ወቅት በለዉሬንስ አግባቢነት ከብሪታንያ ቅኝ ገዢ ጦር ጋር የዘመተዉ የአረብና የኩርዶች ጦር የቱርክን ጦር በየሥፍራዉ ሲገዘግዝ ቆይቶ ጥቅምት 1918 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ደማስቆን ሲቆጣጠር የአረብ-ቱርኮች ጠብ ከረረ።አረቦች ለአዲስ ገዢዎቻቸዉ አደሩ። የዚያኑ ያክል የፍልስጤም እና የኩርድ ሕዝብ የነፃነት ሕልም ቢያንስ እስከ ዛሬ እንደበነነ ቀረ።
አረቦችን ከቱርክ ቀምቶ ለብሪታንያ በብሪታንያ በኩል ለዩናይትድ ስቴትስ ያስረከበዉ ጦርነት ባበቃ በ85ኛ ዓመቱ-በ2003 የቱርኩ ፖለቲከኛ እንደዘበት የወረወሩት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ በርግጥ የለዉም።መልዕክቱ ግን ኢራቅን ከኢራቃዊዉ ገዢ ቀምቶ ለዋሽግተኖች ለማስረከብ፤ አረብን ሐይማኖት፤ ባሕል፤ ከሚጋሩት ቱርኮች ቀምቶ ለብሪታንያዎች፤ በብሪታንያ በኩል ለአሜሪካኖች ያስረከበዉን አይነት ሴራን-የሚያቀነባብረዉ ማነዉ ነዉ-ነበር።ላሁኑ አላወቀንም።
የዋሽግተንና የለንደን መሪዎች በ2003 ኢራቅ ላይ የለኮሱት ጦርነት ግን እስከያኔ-አረብን ከኩርድ፤ ሱኒን ከሺዓ፤ ክርስቲያንን-ከያዚዲ ቀይጣ ታኖር የነበረችዉን ሐብታም፤ ሥልታዊት፤ታሪካዊት ሐገርን የአሸባሪዎች መፈልፈያ፤ የሽብር ቋት፤ የእልቂት አብነት እንዳደረጋት መቀጠሉ ግልፅ-እርግጥም ነዉ።የኢራቅ መጥፋት፤ አንድነቷ መሸራረፍ፤ ሕዝቧ ማለቅ የጀመረበት ስምንተኛ ዓመት ሲዘከር ሶሪያ ላይ የተቀጣጠለዉ የእልቂት ቋያ የመካከለኛዉ ምሥራቅን የታሪክ ጎተራ፤ የዕዉቀት፤ ሥልጣኔ ምድር፤ የአረብ ብሔረተኞችን ማዕከል ከትቢያ እየቀየጣት ነዉ።
ከአምና ጀምሮ ዓለም አቀፍ አሸባሪነቱ ዕለት በዕለት የሚዘገብበት የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS በምሕፃሩ) የፕሬዝደንት በሽር አልአሰድን መንግሥት ያስወግዳል በሚል እምነት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ፤ በማወቅ ይሁን ባለማወቅ ከሪያድ ዶሐዎች ገንዘብ፤ ከቱርኮች መሰልጠኛ ምድር፤ ከምዕራባዉያን ዲፕሎማሲና የጦር ሜዳ ቁሳቁስ ያገኛል ይባል ይባል ነበር።
ቡድኑ የ«ረዳቶቹን» ዜጎችና ወዳጆች «መንደፍ» ሲጀምር ግን በይድረስ ይድረስ የተደራጀዉ ተዘዋዋሪ ትብብር በተቃራኒ ጎዳና ይሾር ያዘ።
ዩናይድ ስቴትስ ዓለምን አስተባብራ አሸባሪዉን ቡድን በጄት መደብደብ ከጀመረችበት አምና ጀምሮ-ቱርክ እንደ አብዛኛዉ ዓለም በተለይም እንደ ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባልነቷ ድጋፍዋን አልነፈገችም።ድጋፏ ግን የአንካራ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ አጥኚ ሁሴይን ባግቺ እንደሚሉት በማለዘብ መርሕ ላይ የተመሠረተ ነበር።
«መንግሥት (የቱርክ)ISISን እንደሚዋጋ አስታዉቋል።ይሕ በምዕራባዉያንና በኔቶ ዘንድ ላለፈዉ ዓንድ ዓመት በግልፅ የሚታወቅ የቱርክ መንግሥት መርሕ ነዉ።ይሁንና በተጨባጭ ቱርክ ባለፉት ሁለት ዓመታት የምትከለዉ የማለዘብ መርሕ ነበር።ምክንያቱም ISIS 49 የቱርክ ዲፕሎማቶችን ከአንድ መቶ ቀናት በላይ አግቶ ነበር።በዚሕም ምክንያት ቱርክ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ነበረች።ይሁንና ዲፕሎማቶቹ ከተለቀቁ በሕዋላ የቱርክ ፀረ- ISIS አቋም በጣም ተጠናክሯል።»
የአንካራ መሪዎች ISISን በመዉጋትና ባለመዉጋት መሐል ቢቃረጡም የደማስቆ ገዢዎችን ለማስወገድ የሚደረገዉን ዉጊያ ከመደገፍ ግን አልቦዘኑም።የረጅም ጊዜ ጠላታቸዉን የኩርድ ሰራተኞች ፓርቲ (PKK) ሲሆን በድርድር፤ ካልሆነም በሐይል፤ የነፍጥ ዉጊያዉን ለማስቆም መጣራቸዉንም አላቋረጡም ነበር።
በቅርቡ ቱርክ በተደረገዉ ምርጫ PKKን ይደግፋል ተብሎ የሚታማዉ የቱርክ ኩርዶች ፓርቲ ያልተጠበቀ ድጋፍ ማግኘቱ፤ ምዕራባዉያን ለኢራቅና ለሶሪያ ኩርዶች በሚሰጡት ሁለንተናዊ ድጋፍ ላይ ሲታከል የኩርድ ነፃነት አቀንቃኞችን የሚያነቃ-ነዉ የሆነዉ።
የቱርክ መንግሥትና ከ1980ዎቹ ጀምሮ በደማስቆና በባግዳድ ገዢዎች እየተረዳ ቱርክን የሚወጋዉ PKK ለሰወስት ዓመታት ያደረጉትን ድርድር በምርጫዉ ማግስት ሲያፈርሱ ከኢራቅ ኩርዶች የተሰማዉ የአንካራን መሪዎች አያሰጋም ማለት አይቻልም።
ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በምዕራባዉያን መንግሥታት ድጋፍ ሰሜን ኢራቅ ኬርቤላ ላይ መንግሥት አከል-አስተዳደር የመሠረቱት የመስዑድ ባርዛኒ ማስጠንቀቂያ «ጌታዋን የተማመነች----» የሚያሰኝ፤ ከጠንካራ ሐገር መሪ ያልተናነሰ ነበር።«ቱርክ የሠላም ስምምነት ሐሳብ አቅርባ PKK ሐሳቡን ዉድቅ ካደረገዉ PKKን ለመቃወም ዝግጁ ነን።ቱርክ PKKን ለማጥፋት በሚል በኛ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች ግን እራሳችንን ለመከላከል ዝግጁዎች ነን»
በዚሕ መሐል ነበር የISIS አባል እንደሆነ የታመነ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቱርክን ከሶሪያ ጋር በሚያዋስነዉ የድንበር ከተማ 32 የቱርክ ዜጎችን አጥፍቶ የጠፋዉ።ዛሬ ሁለት ሳምንቱ።እርምጃዉ አንካራ ከጦርነቱ እንድትገባ፤ ዘላቂ ስልቷንም እንድታጤን፤ ለምዕራባዉያን ግፊት እጇን እድትሰጥም ጥሩ ምክንያት ነዉ የሆነዉ።
ይሁንና የአንካራ መሪዎች ለዘላቂ ጥቅማቸዉ የሚበጀዉን ሳያሰሉ ተንደርድረዉ ከጦርነቱ አልተሞጀሩም።የቱርክ ባለሥልጣናት PKKን ለመቅጣት የሐይል እርምጃ ቢወስዱ ምዕራባዉያን ወዳጆቻቸዉ «እንዳይንጫጩ» በተለይ ከዋሽግተን መተማመኛ መያዝ ነበረባቸዉ።
አንካራዎች የሁለት ግንባር ዘመቻ ለማወጅ እንዲመቻቸዉ የPKK ሸማቂዎችም ሳይተባበሯቸዉ አልቀረም-ቢያንስ በተዘዋዋሪ።የቡድኑ ታጣቂዎች አፈነዱት በተባለ ቦምብ ሰወስት የቱርክ ወታደሮች ተገደሉ።የግድያዉ ለቱርኩ ፕሬዝደንት ለሬሴፕ ጠይብ ኤርዶኻን «ሳይደግስ አይጣላም» አይነት ነበር።«ብሔራዊ ፀጥታችንንና ወንድማዊ አንድነታችንን ከሚያጠቁ ሐይላት ጋር የሠላም ድርድር መቀጠል አይቻልም።»
ወትሮም የፈረሰዉ ድርድር ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ።ጦርነቱ ቀጠለ።የቱርክ የጦር ጄቶች ኩርዶችን ለመምታት ወደ ሰሜን ኢራቅ፤ ISISን ለመዉጋት ወደ ሶሪያ ይከንፉ ያዙ።የቱርክ መንግሥት በቱርኮች ላይ የከፈተዉን ጥቃት አቁሞ ድርድሩን እንዲቀጥል ጀርመንና አንዳድ የአዉሮጳ መንግሥታት መጠየቃቸዉ አልቀረም።ዩናይትድ ስቴትስ ግን የቱርክን እርምጃ ደግፋለች።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሐገራት ዲፕሎማቶችም ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ ባደረጉት ስብሰባ የቱርክን እርምጃ ደግፈዋል።ዋና ፀሐፊ የንስ ሽቶልተንበርግ ከተባባሪያችን ቱርክ ጎን አንቆማለን ነዉ-ያሉት።ያዉም በፅናት።
«ቱርክ ደጃፍ ላይ እና ኔቶ ድንበር አጠገብ ሥላለዉ አለመረጋጋት ለመነጋገር ዛሬ መሰብሰባችን ተገቢ ነዉ።ኔቶ ሁኔታዉን በቅርብ እየተከታተለ ነዉ።ከአባላችን ቱርክ ጎን በፅናት እንቆማለን።»
PKK ጀርመንን ለመሳሰሉ ሐገራት አሸባሪ ድርጅት ነዉ።ጀርመንን ጨምሮ ምዕራባዉያን መንግሥታት ISISን በምድር የሚወጉትን የኢራቅና የሶሪያ ኩርዶችን በቀጥታ፤የቱርክ ኩርዶችን ደግሞ በተዘዋዋሪ ያስታጥቃሉ።ቱርክ ኩርዶችን ትወጋለች፤ ኩርዶችም ቱርክን።ምዕራባዉን መንግሥታት፤ቱርክና አረቦች የደማስቆ ገዢዎችን የሚወጉ አማፂያንን ይደግፋሉ።ISISም የደማስቆ ገዢዎችን ይወጋል።ሁሉም ፀረ-ደማስቆ ናቸዉ።
የባግዳድ ገዢዎች የሳዳም ሁሴንን ቤተ-መንግሥት የተረከቡት ከዋሽግተኖች ነዉ።ዋሽግተን የቴሕራን ጠላት ናት።የባግዳድ ገዢዎች የቴሕራን፤ በቴሕራን በኩል የደማስቆ ወዳጆች ናቸዉ።በዚሕም ሰበብ ባግዳዶች-ደማስቆን አይነኩም።ዋሽግተን፤ ብራስልስ፤ የአረብ ነገስታት፤አንካራ፤-ቴሕራን፤ ደማስቆ፤ባግዳድ፤ ሒዝቦላሕ፤ ኩርዶች ISIS ን ይወጋሉ።ሁሉም የISIS ጠላት ናቸዉ።አንካራ ኩርዶችን ትወጋለች።ዋሽግተን፤ ብራስልስ፤ አረቦች ኩርዶችን ያስታጥቃሉ።የተሳከረ ጦርነት።ግን ሚሊዮኖች ያልቃሉ።ይሰደዳሉ።እስከመቼ-አይታወቅም።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

Saturday, 25 July 2015

ወንጀለኛን (ተጠርጣሪን) የመያዝ አጠቃላይ አካሔድ :: Law

በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ወንጀለኛን (ተጠርጣሪን) የመያዝ አጠቃላይ አካሔድ - Abyssinia law 


በዚህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የወንጅል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር ስለመዋል ወይም ስለመያዝ የሚመለከቱመሠረታዊ ጉዳዮችን ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን የሰዎች የነፃነት መብትና በፖሊስ በወንጀልተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ስለመዋል መካከል ስላለስ ግንኙነት በትንሹ ገለፃ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎችየሚያዙባቸውን መንገዶችና እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ የሚደነግገውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍልበጥልቀት ለመርመር ሙከራ ተደርጓል፡፡
የመያዝና የሕገ መንግሥቱ የነጻነት መብት ግንኙነት
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17 (1) ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ነፃነቱን እንደማያጣ በግልፅይደነግጋል፡፡ ይህም ማለት በንዑስ አንቀጽ (2) እንደተብራራው ማንኛውም ሰው ክስ ሳይቀርብበበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰርእንደማይችል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በሌሎች ሕጎች በግልፅ በተደነገጉ ሁኔታዎች የዜጎች የነፃነት መብት ሊገደብ እንሚችል የሕገመንግሥቱ ‹‹በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ›› የሚለው አገላለፅ ያሳያል፡፡ በመሆኑም  በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ማንኛውም የወንጀል ድርጊት የፈፀመ ሰው ወይም በወንጀል ድርጊት የተጠረጠረ ሰው በፖሊስ የሚያዝበት አግባብ ሊፈጠርእንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡  ይህም ሲሆን ወንጀሉን የፈፀመው ሰው የሕገ መንግሥቱን ዓላማና መንፈስ በጠበቀ መልኩ ነፃነቱመገደቡን መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ በመቀጠል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ እውቅና የተሰጣቸውና በአሁኑ ሰዓትበማገልገል ላይ የሚገኙትን ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶችን እንዲሁም የአያያዝ ሥርዓቶች እንቃኛለን፡፡
በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶች
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ወንጀለኛን በሦስት ዓይነት መንገዶች በቁጥጥር ሥር ማዋል ይቻላል፡፡ እነርሱም የሚከተሉትናቸው፡፡
በፖሊስ መጥሪያ መሠረት ወንጀለኛን መያዝ
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ
ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት ዓይነት ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶች መካከል በፖሊስ መጥሪያ መሠረት የሚደረግ አያያዝ እንደ መርህሲቆጠር የሚቀጥሉት ሁለት መንገዶች በልዩ ሁኔታ የሚተገበሩ (exceptions) ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ በሚከተለው ጽሑፍበወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ለእያንዳንዱ የመያዣ ዘዴዎች የተቀመጡ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡
በፖሊስ መጥሪያ መሠረት ወንጀለኛን /ተጠርጣሪን/ በቁጥጥር ሥር ስለማዋል
የፖሊስ መጥሪያ ማለት በመርማሪ ፖሊስ ተዘጋጅቶ ወንጀሉን ፈፅሟል ተብሎ ለተጠረጠረው ግለሰብ በፖሊስ ጣቢያ እንዲቀርብበዚሁ መርማሪ ፖሊስ አማካኝነት የሚላክ የመጥሪያ ወረቀት ነው፡፡ ለዚህም አግባብነት ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግቁጥር 25 ነው፡፡ ይህ አንቀጽ እንደሚከተለው ይነበባል፡
አንቀጽ25. የተከሰሰውን ሰው ወይም የተጠረጠረውን ሰው ስለመጥራት
አንድ ሰው የወንጀል ስራ መፈፀሙን ለማመን መርማሪ ፖሊስ ምክንያት ያለው ሆኖ በሚገኝባቸው ሁኔታች ሁሉየተባለው ሰው ቀርቦ እንዲጠየቅ ፖሊሱ እንድትቀርብ በሚል በጽሑፍ  ትዕዛዝ ሊጠራው ይችላል፡፡
ስለዚህ በዚህ ሕግ ቁጥር መሠረት በፖሊስ ፊት እንዲቀርብ መጥሪያ የደረሰው ሰው ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ በአንቀጽ 26 በተሰጠውሥልጣን መሠረት መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው እንዲያዝ አስፈላጊውን ርምጃ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን በሕጉ በአንቀጽ 25 መሠረትየመጥሪያ ወረቀት ለመስጠትና የጥሪ ወረቀት ደርሶት በፖሊስ ፊት መቅረብ ያልቻለን ሰው ለመያዝ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎችሊሟሉ የግድ ይላል፡፡
የመርማሪው ፖሊስ በቂ ምክንያት ያለው መሆኑ
ይህም ማለት መርማሪው ፖሊስ መጥሪያ ሊልክለት የተዘጋጀው ሰው ወንጀሉን ፈፅሞታል ብሎ እንዲያምን የሚያስችለው ምክንያትሊኖረው ይገባል፡፡ በሌላ አገላለፅ መርማሪ ፖሊስ ያለምንም በቂ ምክንያት የመጥሪያ ወረቀት በማዘጋጀት መላክ አይችልም፡፡በዋነኛነት የዚህ ቅድመ ሁኔታ አላማ የመርማሪ ፖሊሱን ሥልጣን ገደብ ለማበጀት  ታስቦ የተቀረጸ ይመስላል፡፡ ስለዚህ መርማሪውፖሊስ  መጥሪያ የሚላክለት ሰው ወንጀሉን ፈፅሟል ብሎ እንዲያምን ያደረገውን ምክንያት በዝርዝር እንዲገልፅ ሕጉ ያስገድዳል፡፡
የመርማሪው ፖሊስ ሥልጣን ብቻ ስለመሆኑ
ከዚሁ የሕግ አንቀጽ በቀላሉ እንደምንረዳው ተጠርጣሪውን እንዲቀርብ የማዘዝ ወይም ሳይቀርብ ሲቀር የመያዝ ሥልጣን የተሰጠውለመርማሪ ፖሊስ ብቻ ነው፡፡ ይህንንም ‹‹መርማሪው ፖሊስ›› ተብሎ ከተገለፀው የአንቀጽ 25 ክፍል መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላአገላለፅ ከመርማሪው ፖሊስ ውጭ ያሉ ግለሰቦች ተጠርጣሪውን የመጥራት ወይም የመያዝ ሥልጣን የሌላቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡
የመጥሪያ ትዕዝዙ በጽሑፍ የቀረበ መሆን
ከላይ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ መርማሪ ፖሊሱ የመጥሪያ ትዕዛዙን ሕጉ በሚያዘው መልኩ ማለትም በጽሑፍያዘጋጀ መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለበት፡፡ ከጽሑፍ ውጭ ያሉ የመጥሪያ መንገዶች ለምሳሌ፡-የቃል መጥሪያ በሕጉ ያልተፈቀደበመሆኑ መርማሪው ፖሊስ ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትና የተብራሩት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላትሲችሉ በፖሊስ መጥሪያ መሠረት ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር የማዋል ዘዴ ተግባራዊ መሆን ይችላል፡፡
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለመያዝ
የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ማለት ፖሊስ ተጠርጣሪን እንዲይዝ ያስችለው ዘንድ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የሚሰጥ ሰነድ ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 54 መሠረት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚከተሉትሁለት መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ ያስፈልጋል፡፡
ወንጀለኛውን /ተጠርጣሪውን/ ወደ ፍርድ ቤት ለማቅረብ በሌላ መንገድ የማይቻል መሆኑ
በዚህም መሠረት መርማሪው ፖሊስ ለጥያቄ የፈለገውን ሰው አቅርቦ ለመጠየቅ በማናቸውም መልኩ ያልቻለ እንደሆነ የፍርድ ቤትየመያዣ ትዕዛዝ መጠየቅ ይችላል፡፡ መርማሪው ፖሊስ ተጠርጣሪውን ሊይዝ የሚችልባቸው አመቺና ህጋዊ መንገዶች ካሉ ፍርድ ቤቱየመያዣ ትዕዛዝ መስጠጥ አይኖርበትም፡፡ ለምሳሌ፡- በአንቀጽ 25 መሠረት የመጥሪያ ወረቀት ለተጠርጣሪው በመጀመሪያ ደረጃመላክ ሲችል ይህን ሳያደርግ ቀርቶ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ መጠየቅ አይችልም፡፡
ወንጀለኛው በፍርድ ቤት መቅረቡ ፍፁም አስፈላጊ ሲሆን
ፍርድ ቤቱ የመያዣ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፊት የሰውየው በፍርድ ቤት ወይም በፖሊስ ፊት መቅረብ ፍፁም አስፈላጊ መሆኑንማጣራት ይኖርበታል፡፡ ተጠርጣሪው በፖሊስ ፊት በቅረቡ በብዙ ምክንያቶች የተነሳ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ከነዚህም መካከል፡-ቃልን ለመቀበል፣ ለአካል ምርመራ፣ ለአሻራ ምርመራ፣ ማስረጃዎችን እንዳያጠፋ ለማገድ ወይም ምስክሮች ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድርለማድረግ ተጠርጣሪውን በፖሊስ ወይ በፍርድ ቤት ማቅረብ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜወንጀለኛውን በፍርድ ቤት ማቅረብ  አስፈላጊ የማይሆንባቸው ጊዜዎች አሉ፡፡
ለምሳሌ፡- ጉዳዩ ተከሳሹ በሌለበት (trial in abstentia) በፍርድ ቤት መታየት የሚችል ከሆነ የማያዣ ትዕዛዝ የማይሰጥበት አግባብይኖራል፡፡ ሲጠቃለል ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች መሟላት መርማሪ ፖሊሱ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንዲያገኝናወንጀለኛውን እንዲይዝ ያስችሉታል፡፡
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለመያዝ
የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች፡- የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 21(2) አንዳንድ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ሲፈፀሙ ፖሊሱወንጀለኛውን የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ሳያስፈልገው ሊይዘው እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ወንጀሉ የእጅ ከፍንጅ ከመሆኑበተጨማሪ አንቀጽ 21 (2) እና 50 እንደየቅደም ተከተላቸው የሚከተሉትን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀምጣሉ፡፡
ወንጀሉ የክስ አቤቱታ መቅረብ የማያስፈልገው መሆን
የእጅ ከፍንጅ ወንጀሉ ከ3 ወር በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ መሆን ናቸው፡፡
በዚህም መሠረት ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ሲችሉ በአንቀጽ 50 መሠረት ማንኛውም ሰው ወይም የፖሊስሰራዊት ባልደረባ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲፈፅም የተገኘውን ግለሰብ መያዝ ይችላሉ፡፡
የእጅ ከፍንጅ ያልሆኑ ወንጀሎች፡- የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 51(1) ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀልአድራጊውን የሚያዝበት ሁኔታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ ይህም ማለት ወንጀል አድራጊው ወንጀሉን ሲፈፅም በአካል ያልተያዘቢሆንም እንኳን ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀለኛውን የሚይዝባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ አንቀጽከዘረዘሩት ሁኔታዎች መካከል እጅግ አወዛጋቢና ውይይት የሚያስፈልገው ጉዳይ ቢኖር  በንኡስ አንቀጽ 1 (ሀ) ሥር ተፅፎ የምናገኘውድንጋጌ ነው፡፡ ይህም ቃል በቃል እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
 አንቀጽ 51 (1)
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ መያዝ የሚችለው፡-
ሀ/ ከአንድ አመት በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ለመስራት ዝግጁ የሆነውን ወይም ሰርቷል ተብሎ በሚገባ የተጠረጠረውንሰው፡
በዚህ አንቀጽ መሠረት ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀለኛን ለመያዝ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ፖሊሱ የሚይዘው ሰው ወንጀሉን መፈፀሙን በሚገባ የጠረጠረው መሆን
ወንጀሉ ከአንድ አመት በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ መሆን ናቸው፡፡
ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደምንችለው የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ ወንጀለኛውን /ተጠርጣሪውን/ ለመያዝ የሚያስችል እጅግየተለጠጠ ሥልጣን መጎናፀፋቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም በ1997 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ መሠረት አብዛኛዎቹየወንጀል ዝርዝሮች አንድ አመትና ከዚያ በላይ የሚያስቀጡ በመሆናቸው ይህ አንቀጽ የፖሊስ ባልደረባዎች በብዙ ወንጀሎችያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎችን እንዲይዙ ሊያደርግ ያስችላል ይህ ደግሞ የፖሊስ ባልደረባዎች ስልጣናቸውን በአግባቡናበሕጉ መሠረት እንዳያከናውኑ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
የአያያዙ ሁኔታ
በዚህ ክፍል ፖሊስ ወንጀለኛውን ለመያዝ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ምን ምን ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለበት እንመለከታለን፡፡የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 56 እንደሚያስቀምጠው የመጀመሪያው የፖሊስ ስራ የሚሆነው ለመያዝ የተዘጋጀውንሰው ማንነት በደንብ ለይቶ ማወቅ (ማጣራት) ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በመቀጠል የፍርድ ቤት የመያዝ ትዕዛዝ የተሰጠው እንደሆነይህንኑ ትዕዛዝ ለሚይዘው ሰው ማንበብ ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ይህን የፍርድ ቤት የመያዝ ትዕዛዝ የሚይዘው ሰው የጠየቀውእንደሆነ ማሳየት እንዳለበት ከሕጉ መረዳት እንችላለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች መሟላት ሲችሉ የሚያዘው ሰው  በቃል ወይም እጁን በመስጠት እንዲያዝ ፈቃደኝነቱን ካላሳየ ፖሊሱሰውየውን በመንካት ወይም በመጨበጥ ለመያዝ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚያዘው ሰው አልያዝም ብሎ በሃይል የተከላከለ ወይምለማምለጥ የሞከረ እንደሆነ ሁኔታው በሚፈቅደው ተመዛዛኝ ዘዴ ፖሊሱ ሰውየውን ለመያዝ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄፖሊሱ ሊወስደው የሚችለው ››ተመዛዛኝ ዘዴ›› ምን ያክል ነው?  የሚለው ነው፡፡ ይህም ጥያቄ  መልስ ሊያገኝ የሚችለው ተጠርጣሪየሚያሳየውን ባህሪ ወይም ምላሽ ግምት ውስጥ በማስገባት ስለሚሆን ይህ ነው ብሎ እርግጠኛ የሆነ መልስ መስጠት አይቻልም፡፡