Tuesday, 10 November 2015

የዛሬ 26ዓመት ኖቬምበር 9 ቀን 1989ዓ/ም የበርሊን ግምብ ፈረሰ!




 Kidus Mehalu
የዛሬ 26ዓመት   ኖቬምበር 9 ቀን 1989ዓ/ም የበርሊን ግምብ ፈረሰ!
60 ሚሊዮን ያህል ሰዎች እንዳለቁበት የሚገመተው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲጠናቀቅ ጀርመን ለሁለት ተከፈለች። ማዕከላዊ በርሊንን አልፎ ወደ ምዕራብ ግዛት ለመግፋት የሞከረው የሶቬት ህብረት ሰራዊት የምዕራቡን ክፍል ከተቆጣጠረው የአሜሪካ ጦር ‘ወዴት ነው?’ የሚል ጥያቄ ቀረበለት። ‘ወዴትስ ብንሆን?!’ ብሎ አምልጠው ለአሜሪካ ጦር እጅ የሰጡትን የናዚ ወታደሮች ለመበቀል ያሰፈሰፈው የሶቬት ህብረት ሰራዊት ማዕከላዊ በርሊንን ለቆ ወደ ኋላ እንዲሄድ ተጠየቀ። ሶቬቶች እምቢ ብለው ከአሜሪካ ጋር ጦርነት ውስጥ ሊገቡ ታንኮቻቸውን በማዕከላዊ በርሊን ዝግጁ ማድረግ ሲጀምሩ የሶቬት ህብረት ሊቀመንበር ጆሴፍ ስታሊን ሶቬቶች ወደ ምስራቅ በርሊን እንዲመለሱ እና ወደ ምዕራብ በርሊን የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ እንዲዘጉ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። ይህም በጦርነቱ የተጎሳቆለውን በምዕራብ በርሊን በኩል ያለውን ህዝብ የምግብ አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥበት አደረገ። የምዕራብ በርሊን ህዝብ በርሃብ እና በሞት መሃል ባለበት ሰዓት በአሜሪካዊው ጀነራል ሉዊስ ክሌይ ትዕዛዝ ኦፕሬሽን ቪትልስ ተጀመረ። ኦፕሬሽን ቪትልስ የአሜሪካ አውሮፕላኖች በየቀኑ የምግብ፣ቅቤ፣ለውዝ፣ስጋ፣
ቫይታሚን፣ቸኮሌት እና ማስቲካ ለምዕራብ በርሊን ነዋሪዎች ለ15 ወራቶች ያህል ከ277ሽ የሚበልጥ በረራ በማድረግ ከሰማይ ላይ እየወረወሩ ህዝብ ሲቀልቡበት የነበረ ፕሮግራም ነው።

ነሃሴ 13 ቀን 1961ዓ/ም በስምራቅ በርሊን በኩል ሶቬት ህብረት የበርሊን ግምብን መስራት እንደጀመረች 50ሽ ያህል የምስራቅ በርሊን ሰራተኞች በምዕራብ በርሊን ካላቸው የስራ ገበታቸው ላይ መሄድ እንዳይችሉ ተደረገ። ይህ ግምብ ወደ ምዕራብ ጀርመን የሚሄዱ የምስራቅ ጀርመንን ሰዎች ለማገድ የተሰራ ሲሆን ለ28ዓመታት ያህል ቆሟል። የዛሬ 26ዓመት ኖቬምበር/ህዳር 4 ቀን 1989ዓ/ም ምስራቅ በርሊን ዓይታው የማታውቀው ዓይነት የህዝብ አመጽ አስተናገደች። እዚህም እዚያም በሚነሱ የነጻነት ጥያቄዎች እርስ በርስ መስማማት ያልቻሉት የምስራቅ ጀርመን መሪዎች ስብሰባ ተቀምጠው እንዴት እና በምን መልኩ ለህዝቡ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው መምከር ይዘዋል። ይሄው ምክክር እስካሁን የት እንደደረሰ እና በቀጠይ ቀናት ስለምን እንደሚመክር ለመግለጽ የምስራቅ ጀርመን ሶሻሊስት ዩኒቲ ፓርቲ ፖሊት ቢሮ አባል የሆኑት ጉንተር ሻቦውስኪ ከምሳቅ እና ምዕራብ በርሊን እንዲሁም ከጣሊያን እና ከስፔይን ከተወጣጡ ጋዜጠኞች ፊት ተቀምጠዋል። በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈውን የጉንተር ሻቦውስኪ ገለጻ ህዝቡ ለማዳመጥ በቴሌቪዥን ስር አፍጥጧ። ኖቬምበር 9 ቀን 1989ዓ/ም!

ሪካርዶ ኤህርማን የሚባል ለጣሊያን ዜና አገልግሎት የሚሰራ ጋዜጠኛ ባለስልጣኑን “የምስራቅ ጀርመን ህዝብ የመጓዝ እና ወደ ሌሎች ሃገራት የመንቀሳቀስ ነጻነቱን ለማክበር የወሰናችሁት ነገር አለ ወይ?” በማለት ጠየቀ።በቃላቸው ቀጥተኛ ምላሽ መስጠት ያልቻሉት ባለስልጣኑ ከያዙት ወረቀቶች ውስጥ አንድኛውን ለይተው በማውጣት “የምስራቅ ጀርመን ዜጋ ሁሉ ማንንም ሳያስፈቅ እና የፖሊስን ይሁንታ ሳይጠይቅ ወደ ምዕራብ ጀርመን ሊሄድ ይችላል።”በማለት አነበቡ። ሌላ ጋዜጠኛ ቀጠለና “ከመቼ ጀምሮ?”ብሎ ባለስልጣኑን ጠየቃቸው። ለዚህ የሚሆን መልስ በያዟቸው ወረቀቶች ውስጥ እንደሌለ የተረዱት ባለስልጣኑ “እኔ እንደሚመስለኝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ፤አሁኑኑ!”በማለት ግራ እየተጋቡ ምላሻቸውን ሰጡ። ይህን የባለስልጣኑን ምላሽ ያደመጡት ነጻነትን ፍለጋ ወደ ምዕራብ ጀርመን ለመግባት ለ28ዓመታት ያህል የበርሊንን ግምብ ሲዘሉ እና ለመዝለል ሲሞክሩ የኖሩ የምስራቅ ጀርመን ሰዎች ባለስልጣኑ ንግግሩን እስኪጨርስ ማድመጥ ሳያስፈልጋቸው ዶማ፣መዶሻ፣ እና ሌሎች ግምብ ለማፍረስ የሚረዱ ንገሮችን ይዞ ወደ በርሊን ግምብ ተመሙ። ልክ የዛሬ 26ዓመት በዛሬው ዕለት የባርነት፣የመለያየት፣የውርደት፣የኋላ ቀርነት ተምሳሌት ተደርጎ ሲቆጠር የኖረው የሶሻሊስቱ ዓለም ምልክት በበርሊን ህዝብ ፈረሰ። የበርሊን ግምብ መፍረስ በአውሮፓ ሲያጣጥር የኖረው ሶሻሊዝም ውድቀት አይቀሬ መሆኑ ተረጋገጠ።

በዘመነ ደርግ ቡና በጥሬው ካልሰጣችሁን ለኤርትራ የጦር ድጋፍ እንደርጋለን ሲሊ የኖሩት፣ብሄራዊ ባንክን 5ነጥብ 6ሚሊዮን ዶላር ያጭበረብሩት፣ ‘አይፋ’ የተባለውን መኪና በግድ በቡና ካልቀየራችሁን እያሉ እጅ ሲጠመዝዙ የኖሩት፣ ከኢትዮጵያ ቡና ወስደው አየርባየር ለደቡብ ኮሪያ እየሽጡ ከዚያው ለኢትዮጵያ ወታደሮች ልብስ እየሸመቱ የምስራቅ ጀርመን ምርት አስመስለው ሲያታልሉ የኖሩት የምስራቅ ጀርመን ሶሻሊስቶች በመጨረሻው ሰዓት በህዝብ የነጻነት ትግል ተሽነፉ። ከሶቬት ህብረት ቀጥላ ዋናዋ ወዳጃችን የነበረችውን ሃገር እና አይፋ ለሚባለው መኪናቸው ኢትዮጵያዊያን ‘አይፋ ለናት ሃገሩ ተደፋ’ የተባለላትን ምስራቅ ጀርመንን ሶሻሊዝም በአፍጢሟ ደፋት። የበርሊን ግምብ በፈረሰበት ወቅት የሶሻሊስት ስርዓት አራማጅ በነበረችው ምስራቅ ጀርመን ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ የለም ነበር። በአንጻሩ ካፒታሊስቷ ምእራብ ጀርመን በኢኮኖሚ አቅሟ ከአሜሪካ ቀጥላ ከዓለም ሁለተኛ ነበረች። የበርሊን ግምብ ከፈረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ እኤአ ጥቅምት 3ቀን 1990ዓ/ም ለ41ዓመታት ለሁለት ተከፍላ የነበረችው ጀርመን እንደገና አንድ ሃገር ሆነች። በማዕከላዊ በርሊን ከሚገኘውና በጀርመን ሃገር በተነባቢነቱ፣በተፈላጊነቱ እንዲሁም በግዙፍነቱ አንደኛ በአውሮፓ ደግሞ ሁለተኛ ከሆነው የሚዲያ ተቋም ህንጻ ጫፍ ላይ ሆኘ ያነሳሁትን ፎቶ የበርሊን ግምብ ቆሞበት የነበረውን ስፍራ የሚያሳየውን አካባቢ [በቀዩ ቀስቶች መሃል ያለው] ታዩት ዘንድ ከታች ለጥፌላችኋለሁ። ስፍራው እንደምታዩት አሁን ዝንጥ ያሉ ህንጻዎች ተሰርተውበታል። የበርሊን ግምብ ከመፍረሱ በፊት ምን ይመስል እንደነበር ግን ለታሪክ እና ለማስታወሻ ከቀረው የግምቡ ቅሪት ስር የተነሳሁትን ፎቶ በኮሜንት ሳጥን ላይ ስለለለጠፍኩት ማየት ይችላሉ። 
If You want to see the writers Page :-  Kidus Mehalu






Sunday, 1 November 2015

አስደንጋጩ የደቡብ ሱዳን ግምገማ

  ፓለቲካ - አስደንጋጩ የአፍሪካ ኅብረት የደቡብ ሱዳን ግምገማ

አስደንጋጩ የአፍሪካ ኅብረት የደቡብ ሱዳን ግምገማ ዋና ዜና
01 November 2015 ተጻፈ በ 
Source :- Ethiopian Reporter
Posted By : Abiy Abebe 

አስደንጋጩ የአፍሪካ ኅብረት የደቡብ ሱዳን ግምገማ

ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች ሉዓላዊ አገር ሆና ብቅ ያለችው እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2011 ነበር፡፡ ደቡብ ሱዳናውያን ይህን ነፃነት ለመቀዳጀት እ.ኤ.አ. ከ1956 ጀምሮ ከሰሜን ሱዳናውያን ጋር ጦርነት ውስጥ ቆይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1977 በደቡብ ምዕራብ ሱዳን ነዳጅ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ፣
የእርስ በርስ ጦርነቱ ይበልጥ ተጧጡፎ ቀጠለ፡፡ እ.ኤ.አ. በ1983 በኮሎኔል ጆን ጋራንግ አማካይነት የሱዳን ሕዝቦች ነፃ አውጭ ጦር መቋቋም ትግሉን ይበልጥ የተደራጀ አደረገው፡፡
ለግማሽ ክፍለ ዘመን በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ለቆየችው ሱዳን እ.ኤ.አ. በግንቦት 2005 የተፈረመው ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት የለውጥ መሠረት ተደርጎ ተወስዶ ነበር፡፡ ይህ ስምምነት ደቡብ ሱዳን በስድስት ዓመታት ውስጥ ነፃ አገር የምትሆንበትን አካሄድም የነደፈ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት እ.ኤ.አ. ከጥር 9 እስከ ጥር 15 ቀን 2011 በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ ደቡብ ሱዳናውያኑ ነፃነታቸውን መረጡ፡፡
ነፃነቱ ከሱዳን መንግሥት ጋር የነበረውን አተካሮ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በር የከፈተ ቢሆንም፣ ከጋራ ጠላታቸው ከካርቱም ጋር የተባበሩት የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች የውስጥ ችግር ለማገርሸት ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የፈጀው፡፡ ይህ ልዩነት እየተባባሰ መጥቶ ነፃነቱ ያመጣዋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን ለውጥ እያጨለመው መጣ፡፡ ደቡብ ሱዳን ከነፃነትም በኋላ ከሱዳን ጋር ያላት ውጥረት የተለያየ ገጽታ እየያዘ ቢቀጥልም፣ በራሳቸው በደቡብ ሱዳናውያን መካከል የተከሰተው አለመግባባት ሌላ መጠነ ሰፊ ስቃይና መከራ ያስከትላል ብሎ የገመተ ብዙም አልነበረም፡፡
በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና በምክትላቸው ዶ/ር ሪክ ማቻር መካከል ያለው ልዩነት ወይ ይፋ ጦርነት ያመራው እ.ኤ.አ. በታኅሳስ 2013 ነበር፡፡ ፕሬዚዳንቱ የዶ/ር ማቻር ታማኝ ወታደር ናቸው ባሏቸው አካላት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጎብኛል ማለታቸውም ይታወሳል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ በደቡብ ሱዳን መንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ. ከጥር 2014 ጀምሮ በተለያዩ ዙሮች ድርድሮች ቢካሄድም እስካሁንም ችግሩ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡ በየጊዜው የሚፈረሙ የተኩስ አቁም ስምምነቶችም በሰዓታት ልዩነት መጣሳቸው ለደቡብ ሱዳን አዲስ ነገር መሆኑ አቁሟል፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ የሚመረምር ኮሚሽን እንዲቋቋም ወሰነ፡፡ ኮሚሽኑ በደቡብ ሱዳን ግጭት ወቅት የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ተገቢነት የሌላቸው ሌሎች ድርጊቶች እንዲመረምር፣ የጥሰቶቹን መነሻዎች እንዲለይ ግጭቶቹና ጥሰቶቹ ዳግም እንዳይከሰቱ በሚያስችል ሁኔታ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፣ እርቅ መፍጠርና ጠባሳዎችን ለማዳን የሚያስችሉ ምክረ ሐሳቦችን እንዲሰጥና ደቡብ ሱዳንን ወደ አንድነት፣ ትብብርና ዘላቄ ልማት የሚወስዱ መንገዶችን እንዲጠቁም ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር፡፡
መጀመሪያ ላይ ኮሚሽኑ ሪፖርቱን በሦስት ወራት ውስጥ እንዲያስረክብ ተወስኖ ነበር፡፡ ይሁንና የተሰጠውን ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት የተሰጠው ጊዜና በጀት በቂ እንዳልሆነ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ በአጠቃላይ የኮሚሽኑ አባላት አምስት ሲሆኑ፣ ከኦባሳንጆ በተጨማሪ ዕውቁ ኡጋንዳዊ ተማራማሪ ማህሙድ ማምዳኒም ተካተዋል፡፡ ኮሚሽኑ የሪፖርቱ ጊዜ ከተራዘመለት በኋላ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 15 ቀን 2014 ለአፍሪካ ኅብረት ያቀረበ ቢሆንም፣ ሪፖርቱ ይፋ ሳይደረግ ቆይቶ ከቀናት በፊት ይፋ ሆኗል፡፡
‹‹በሪፖርቱ የተካተቱትን ዝርዝርና አንገብጋቢ ጉዳዮች ካየን ለምን ተጨማሪ ጊዜ እንደወሰደ መገመት አይከብድም፡፡ ሪፖርቱ ጉዳዮችን በጥልቀትና በዝርዝር የዳሰሰ ሲሆን፣ በደቡብ ሱዳን ውስጥ ያሉና ከዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት አካላት ጋር ምክክር በማድረግ፣ በግጭቱ የተሳተፉ ተገዳዳሪ ወገኖችን በማሳተፍ፣ ፖለቲካዊ ስሱ የሆኑ ጉዳዮችን ያካተተ ከመሆኑ አንፃር ለምን ዘገየ የሚለው እንደ ጉዳይ ባይታይ እመርጣለሁ፤›› ያሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም መምህርና በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሰንዴይ ኦኬሎ ናቸው፡፡
ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2014 ሥራውን ከጀመረ በኋላ ተከሰቱ የተባሉ ወንጀሎችንና የመብት ጥሰቶችን የመረመረ ሲሆን፣ በዚህም የዓይን እማኞችን ጨምሮ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሯል፡፡
በማስገደድ ሰው ሰውን እንዲበላ ማድረግና ሌሎች አሰቃቂ ድርጊቶች ተፈጽመዋል
የኮሚሽኑ ሪፖርት ከተጠናቀረ በኋላ የሁለቱ ወገኖች ግጭት ባለፉት 15 ወራት አለመቀዝቀዙን የሚጠቁሙ መረጃዎች ተሠራጭተዋል፡፡ ይሁንና በሪፖርቱ የተካተቱ የመብት ጥሰቶች ለብዙዎች እጅግ አስደንጋጭና እንቅልፍ የሚነሱ ሆነዋል፡፡ ሰዎች ተገደው ሰው እንዲበሉ መደረጋቸው የዓለም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ የቡድን አስገድዶ መድፈር፣ በቁም በማቃጠል ግድያ መፈጸም፣ ግርፋትና ኢሰብዓዊ አያያዝ ከእነዚህ አሰቃቂ ድርጊቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች በሁለቱም ወገኖች መፈጸማቸው በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በአሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከአገራቸው ለመሰደድ መገደዳቸውም ተመልክቷል፡፡
ለደቡብ ሱዳን ግጭት አዲስ ክስተት ባይሆንም የኮሚሽኑ አባላት ያነጋገሯቸው ደቡብ ሱዳናውያን በዚህ መጠንና ዓይነት የመብት ጥሰቶችን ከዚህ ቀደም ሲል አለመመልከታቸውን መግለጻቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ በተለይ ሰላማዊ ዜጎችን የጥቃት ሰለባ ማድረግ አዲስ ክስተት እንደሆነ መናገራቸውም ተጠቅሷል፡፡
በሁለቱም ወገኖች በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተመሳሳይ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የዘረዘረው ሪፖርቱ፣ በተለይ በጉደሌ እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 16 ቀን 2013 የተፈጸመው ድርጊት የግጭቱን ገጽታ በሚገባ የሚያሳይ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ በዚያች ዕለት የሳልቫ ኪር ወታደሮች ዶ/ር ማቻርን ይደግፋሉ የተባሉትን የኑዌር ብሔር አባላትን በማስገደድ የሰው ደም እንዲጠጡ፣ የሰው ሥጋ እንዲበሉና ወደሚንበለበል እሳት ተወርውረው እንዲገቡ በማድረግ ማስገደላቸውን ከዓይን እማኞች ማረጋገጡን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ የሁለቱ ወገኖች ጦር ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግን መጣሱንም አካቷል፡፡ ጥቃቱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከማተኮሩ በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያናት፣ መስጊዶች፣ ሆስፒታሎችና ከተሞች መውደማቸውንና የሰብዓዊ ዕርዳታዎች መስተጓጎላቸውን፣ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት እንዲሳተፉ መደረጋቸውንም አብራርቷል፡፡
ከእነዚህ ድርጊቶች አንፃር የጦር ወንጀሎችና በሰብዓዊነት ላይ የሚቃጡ ወንጀሎች መፈጸማቸውን መደምደም እንደሚቻልም አመልክቷል፡፡ ይሁንና በግጭቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ኮሚሽኑ በቂ መረጃና ምክንያት አለማግኘቱን አስገንዝቧል፡፡
ከአጠቃላይ ሁኔታዎች ለመረዳት እንደሚቻለው የተከሰቱት ጥሰቶች በተቀናጀ ሁኔታ የተከናወኑ በመሆናቸው፣ ሰላማዊ ግለሰቦችን በብሔራቸው ወይም በፖለቲካ አቋማቸው  የተነሳ ጥቃት እንዲደርስባቸው የማድረግ ፖሊሲን መንግሥት ተከትሏል ብሎ መደምደም እንደሚቻልም ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡
ተጠያቂነትን ማረጋገጥ
ኮሚሽኑ ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂነትን እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ ቅድሚያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች በመስጠት መመርመሩን ገልጿል፡፡ በዚህም ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የሚቻለው ሰላምን ሳያደፈርሱና ለደቡብ ሱዳን አዲስ ጅማሮ አረጋግጦ መሆን እንዳለበት አስተያየት ከአብዛኛው ዜጋ እንደተሰጠው አመልክቷል፡፡
ይህ ማለት ድርጊቶችን የፈጸሙ ግለሰቦች ተጠያቂ አይሁኑ ማለት እንዳልሆነ ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ በደቡብ ሱዳን የገነነውን ከተጠያቂነት የማምለጥ ባህል እንዲገረሰስ የሕዝቡ ፍላጐት እንደሆነ አመልክቷል፡፡ ይሁንና ይህ የወንጀል ተጠያቂነት ዕርቅንና ዘላቂ ሰላምን ሳይገፋ መከናወን እንዳለበት አስገንዝቧል፡፡ በሁለቱም ወገኖች ያሉ አብዛኛዎቹ በኮሚሽኑ አባላት የተጠየቁ ዜጐች በግለሰብ ደረጃ ፕሬዚዳንቶች ሳልቫ ኪርና ተቀናቃኛቸው ዶ/ር ሪክ ማቻር ለተከሰተው ቀውስ፣ ለመባባሱና ለደረሰው የመብት ጥሰት ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው መናገራቸውም ተጠቅሷል፡፡ ምን ዓይነት ተጠያቂነት የሚለው ከተሰጡት ምላሾች መረዳት ባይቻልም የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና የፖለቲካ ወይም አስተዳደራዊ ተጠያቂነትን በማቀላቀል መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ መክሯል፡፡
መላሾቹ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በተለይ ከፍተኛ የፖለቲካና የወታደራዊ መሪዎችን በተመለከተ በብሔራዊ የፖለቲካና የፍትሕ ተቋማት ላይ መተማመን የሌላቸው በመሆኑ በአፍሪካ የሚመራ፣ በአፍሪካውያን ባለቤትነት የሚካሄድና በአፍሪካ ሀብትና የሕግ ማዕቀፍ የሚመራ፣ በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚታገዝና የደቡብ ሱዳን ዳኞችና ጠበቆች የሚሳተፉበት አሠራር ተግባራዊ እንዲሆን ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል፡፡
ኮሚሽኑ ከፍትሕና ከዕርቅ ቅድሚያ ለየቱ ይሰጥ የሚለው ጥያቄ በውጥረት የተሞላ መሆኑን አስታውሶ፣ ለደቡብ ሱዳን ችግር መፍትሔ ለመስጠት የእያንዳንዱን ችግር ዓውድ በማጥናት የተለያዩ መፍትሔዎችን በመቀላቀል መጠቀም እንደሚችል አመልክተዋል፡፡ የዚህ ሒደት መጀመር ያለበት የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀያቸው በመመለስ መሆን እንዳለበትም አስገንዝቧል፡፡
ኮሚሽኑ ችግሩን ለዘለቄታው ለመቅረፍ የእውነትና የዕርቅ ኮሚሽን መቋቋም እንዳለበትም ሐሳብ አቅርቧል፡፡ የሚቋቋመው ኮሚሽን ወደፊት በሚደረጉ ምክክሮች በሚወሰነው ጊዜ ውስጥ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በማጣራት እውነት እንዲወጣ፣ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲመጣ፣ ይቅር ባይነት እንዲኖር፣ ተጠቂዎችን ወደ ቦታቸው ለመመለስ ጥሪ እንዲደረግ በመሥራት ፍትሕና ዘላቂ ዕርቅ እንዲፈጠር ማድረግ እንዳለበት ምክረ ሐሳቡ ያብራራል፡፡
ከኮሚሽኑ አባላት መካከል ፕሮፌሰር ማሕሙድ ማምዳኒ በጻፉት የተለየ አስተያየት፣ ፍትሕንና ዕርቅን ለመቀላቀል ተግባራዊ ለማድረግ አራት ወሳኝ ጉዳዮች ግንዛቤ ውስጥ ሊገቡ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ እነዚህም ከተጠያቂነት የማምለጥ ባህል፣ የተጠያቂነትን ትርጉም መረዳት፣ የፖለቲካዊ ሒደት አስፈላጊነትን መረዳትና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደርን እንዴትና መቼ እንጠቀማለን? የሚለውን መለየት ናቸው፡፡
ፕሮፌሰር ማምዳኒ አይሲሲን መሰል ተቋማት የሚከተሉት የምዕራባውያን የፍትሕ አረዳድ ለአፍሪካ አዋጭ አይደለም ብለው ከሚከራከሩ ምሁራን አንዱ ናቸው፡፡ በዚህም አስተያየታቸው ‹‹አፍሪካዊ መፍትሔ›› ያሉትን አካሄድ ሲያብራሩ ምዕራባውያን የእኛ መፍትሔ የትም የሚሠራ ነው፣ ለሁሉም የሚስማማ ነው በማለት ያደረሱትን ጥፋት በመዘርዘር ነው፡፡ ምዕራባውያኑ ደቡብ ሱዳን ከነፃነቷ በፊት ራሷን የማስተዳደር ታሪክ እንደሌላትና የተፈተኑ ተቋማት እንደሌላት እየታወቀ ‹‹ምርጥ ተሞክሮዎች›› በመቅዳት ደቡብ ሱዳንን ለመገንባት መሞከር የዚህ ችግር ማሳያ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ከተጠያቂነት አንፃር ወንጀል ከተፈጸመ አጥፊውን መቅጣት ነው በሚል ጉዳዮችን የወንጀልና የቅጣት ጉዳይ አድርገው አቅለው እንደሚመለከቱም አመልከተዋል፡፡
ድጋፍና ተቃውሞዎች
‹‹ይህ ሪፖርት ከአፍሪካ ኅብረት ከመምጣቱ አንፃር ታሪካዊ የሚባል ነው፡፡ መሰል ሪፖርቶችን የምናገኘው ከሒውማን ራይትስ ዎች፣ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናልና መሰል ተቋማት ነበር፡፡ ሪፖርቱ በጣም ሸንቋጭና ጥፋቶችን በግልጽ የሚዘረዝር መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች ለደረሰው ጭፍጨፋ የሞራል ከተቻለም የወንጀል ተጠያቂነትን ለሰላም ሲሉ መቀበል አለባቸው፡፡ ይሁንና የደረሰው ጭፈጨፋ ደረጃ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚጠይቅ ነው፤›› በማለት ለሪፖርተር በጽሑፍ አስተያየታቸውን የሰጡት መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉት የሰላምና ደኅንነት ተንታኝና ተመራማሪ  አቶ ዓለማየሁ ፈንታው ናቸው፡፡
በተመሳሳይ ዶ/ር ሰንዴይ ሪፖርቱ አስደንጋጭ የሆኑ ግኝቶችን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ፣ ግልጽ ማብራሪያ በመስጠትና ምከረ ሐሳብ በመስጠት ሕያው ሰነድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ ኅብረት ከሚከተለው መርህና የሥነ ምግባር ደንብ አኳያ ጉዳዩን መመርመሩንም አመልክተዋል፡፡ ‹‹የችግሩን መነሻ፣ የተከሰተው ነገር ምን እንደሆነ? መፍትሔው ምን እንደሆነ? በዝርዝርና በግልጽ ያስቀመጠ ሪፖርት ነው፡፡ የአፍሪካ ኅብረትም ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ የተከሰተው ነገር ድጋሚ እንዳይከሰት ምን መደረግ አለበት? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚረዳ ነው፡፡ ሰነዱን በሚገባ በመመርመርና በመፈተሽ የመፍትሔው አካል መሆን እንጂ ስሜታዊ በመሆን ለሌላ በቀል የሚጋብዘን መሆን የለበትም፤›› ብለዋል፡፡
ሪፖርቱ በደቡብ ሱዳንም የተለያዩ የድጋፍና የተቃውሞ አስተዳደሮችን እያስተናገደ ነው፡፡ ጥቅምት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ሪፖርቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ የደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ መብት ውትወታ ማኅበረሰብ ባወጣው መግለጫ፣ ሪፖርቱ በደቡብ ሱዳን ሰላም ለማምጣት ወሳኝ ነው ብሏል፡፡ ‹‹የተከሰቱትን ጭፍጨፋዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ ክህደትና መነቃቀፍ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ለተፈረመው የሰላም ስምምነት መፈጸም የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል፤›› ብሏል፡፡
በተመሳሳይ ዘ ኮሙዩኒቲ ኢምፓወርመንት ፎር ፕሮግረስ ኦርጋናይዜሽን የተባለው ሲቪል ማኅበር፣ ሪፖርቱ የአፍሪካ ኅብረት ለፍትሕ የሚሠራ ተቋም መሆኑን የሚያሳይ ታሪካዊ ሰነድ እንደሆነ ገልጿል፡፡ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤድመንድ ያካኒ ሁለቱ ወገኖች በሪፖርቱ ለቀረባቸው ወቀሳ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሪፖርቱ ቅሬታ የቀረበባቸውና ተጠያቂ የተደረጉት ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ ቱት ጋትልዋክ ሪፖርቱን ‹‹መሠረተ ቢስ›› ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ በተለይ የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ኃይሎች በኑዌር ብሔር አባላት ላይ ጥቃት የፈጸሙት በመንግሥት ፖሊሲ ነው መባሉ እውነትነት የሌለው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሪፖርቱ ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከተጠያቂነት በተጨማሪ በ315 ገጾች በተቋማት ይዞታ ላይ፣ በአስተዳደር ሥርዓቱ በተለይ በፌዴራል የመንግሥት መዋቅሩ ላይ፣ በፀጥታ ዘርፍና በፖሊስ ላይ፣ በፋይናንስ አስተዳደር ላይ፣ በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓቱ ላይ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪል ማኅበራትና በሚዲያ ሚና ላይ ጥልቅ የሆነ ትንተና ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡
በርካታ ተንታኞች በሪፖርቱ አቀራረብና ይዘት ላይ ቅሬታ የሌላቸው ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳንን ችግር ለመቅረፍ መቼና እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል? በሚለው ላይ ግን ያላቸውን ጥርጣሬ አስፍረዋል፡፡
Source :- Ethiopian Reporter
Posted By : Abiy Abebe

Tuesday, 27 October 2015

New Access Point to Use FREE Internet in Ethiopia

New Access Point to Use FREE  Internet  in Ethiopia .

Updated: This setting helped us to use free 3G Internet in our mobile for more than two weeks. Unfortunately, this setting is not working at this moment. Ethio telecom might change the proxy and once we found a new proxy, we will post an update here.

Fill all the parameters as shown below:
Name: mms
APN: et.mms
APN type: default
Proxy: 10.204.189.211
Port: 9028
Username: Not set
Password: Not set
Server: Not set
MMSC: 10.204.181.76:80/was
MMS Proxy: Not set
MMS Port: Not set
MCC: 636
MNC: 01
Authentication type: Not set
APN Protocol: IPv4
APN roaming protocol: IPv4
APN enable/disable: APN enable
Bearer: unspecified
MVNO type: None
MVNO value: Not set

NOTE :- If this setting is not work,  Ethio telecom might change the proxy and once we found a new proxy, we will post an update here.
#Free_Internet , Internet in Ethiopia ,3G internet , Ethiopian Access Point

Saturday, 24 October 2015

የመንግስት የውጭ ብድር፤ 19 ቢሊዮን ዶላር (390 ቢ. ብር) ደርሷል . Abiy1702

የመንግስት የውጭ ብድር፤ 19 ቢሊዮን ዶላር (390 ቢ. ብር) ደርሷል 

ጠቅላላ የመንግስት ብድር ( የአገር ውስጥ ብድርም ጭምር) ወደ 700 ቢሊዮን ብር ገደማ ሆኗል! Abiy1702

Written by  ዮሃንስ ሰ. (Source Addis Admas News Paper )
 ጠቅላላ የመንግስት ብድር፣ ወደ 700 ቢሊዮን ብር ገደማ ሆኗል!
• በ2002 ዓ.ም፣ የውጭ ብድር፣ 5.6 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ነበር።
• አሁን፣ የውጭ ብድር፡ ከሁለት እጥፍ በላይ ጨምሯል - 19 ቢሊዮን ዶላር።
• በ2002 ዓ.ም፣ ለውጭ እዳ 111 ሚ.ዶ ተከፍሏል (ባሁኑ ምንዛሬ 2.3ቢ. ብር)።
• አምና፣ የውጭ እዳ ክፍያው 970 ሚ.ዶ ነበር (ከ14 ቢ. ብር በላይ)።
• በ2002 ዓ.ም፣ የዓመት ወለድ 42 ሚ.ዶ ነበር (ባሁኑ ምንዛሬ ከ1ቢ. ብር በታች)።
• አምና፣ የዓመት ወለድ 250 ሚ.ዶ ተከፍሏል (ከ5 ቢ. ብር በላይ)።

የመንግስት የውጭ ብድር፣ 19 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሰሞኑን ያወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል። አብዛኛው ብድር፣ ለባቡር ትራንስፖርት፣ ለቴሌ እና ለመንገድ ግንባታ የሚውል ቢሆንም፤ የብድር መጠኑ በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ነው በማለት የአለም ባንክና የአይኤምኤፍ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ከአምስት ዓመት በፊት፣ የውጭ ብድር ለመመለስ፣ አገሪቱ 111 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ከፍላለች። አምና ግን፣ የብድር ወለድ ብቻ፣ ሩብ ቢሊዮን ዶላር (250 ሚ.ዶ) ደርሷል። ወለዱን ጨምሮ፣ ለእዳ ክፍያ የዋለው የውጭ ምንዛሬ ደግሞ፣ 970 ሚ.ዶ ነው ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት።
የመንግስት ብድር እና የእዳ ክፍያው፣ ባለፉት አምስት ዓመታት፣ ከሁለት እጥፍ በላይ የጨመረው፣ ለትልልቅ ፕሮጀክቶች የሚመጣ ብድር በመብዛቱ እንደሆነ አይኤምኤፍ ገልጿል።
በእርግጥ፣ ካሁን በፊትም፣ በተለይ እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ፣ እንደ በርካታ የአፍሪካ አገራት፣ ኢትዮጵያም ከፍተኛ የብድር እዳ ተከማችቶባት እንደነበር ይጠቅሳል አይኤምኤፍ። በዓመት፣ ከኤክስፖርት የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ብቻ በነበረበት በዚያ ወቅት፣ የአገሪቱ የብድር እዳ ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ እንደነበር ይታወሳል። አብዛኛው እዳ የተቃለለውም፣ በብድር ስረዛ ነው። በሚሌኒዬሙ መባቻ ላይ የእዳ ክምችቱ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በታች ወርዶ እንደነበር የአይኤምኤፍ መረጃ ያሳያል። ግን እዚያው አልቆየም።
ከነባሮቹ አበዳሪዎች በተጨማሪ፣ ለቴሌኮሙኒኬሽን ማስፋፊያ ከቻይና የመጣ ብድር እንዲሁም፣ ለመጀመሪያዎቹ የስኳር ፕሮጀክቶች የህንድ ብድር ታክሎበት፣ በ2002 ዓ.ም የመንግስት የእዳ ክምችት፣ ወደ 5.6 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። ከዚያ ወዲህ፣ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አማካኝነት የተጀመሩት በርካታ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ደግሞ፣ የመንግስትን እዳ በሁለት እጥፍ እንዲጨምር አድርገዋል - በተለይም ከአዳዲስ አበዳሪዎች።
ከትልቁ ነባር አበዳሪ፣ ከአለም ባንክ የሚመጣ ብድር ቀንሷል ማለት አይደለም። ወደ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገደማ የነበረው የባንኩ የብድር ክምችት፣ አምና 4.5 ቢ. ዶላር ደርሷል። የአፍሪካ ልማት ባንክና ፈንድ ሲጨመርበት ስድስት ተኩል ቢሊዮን ዶላር ሆኗል - የብድር ክምችቱ። እነዚህ ነባር አበዳሪዎች ናቸው።
ግን አዳዲሶቹ አበዳሪዎችም አሉ - በተለይ ቻይና። የቻይና ብድር፣ ሁለት ዓይነት ነው። በቀጥታ የሚመጣ ብድር አለ - ለምሳሌ ለባቡር መስመር ግንባታ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ በዜድቲኢና በሁዋዌ አማካኝነት፣ ለቴሌኮም ማስፋፋፊ የሚመጣ ብድር አለ። ሌሎቹ አዳዲስ አበዳሪዎች፣ ህንድ (ለምሳሌ ለስኳር ፕሮጀክቶች)፣ እንዲሁም ቱርክ (ለባቡር መስመር ዝርጋታ) ይጠቀሳሉ። ከእነዚህ አገራት የመጣ የብድር ክምችት፣ በ2002 ዓ.ም፣  ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በታች ነበር። አምና ግን፣ የእነዚሁ የብድር ክምችት፣ 8.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ሆኗል።
የነባሮቹና የአዳዲሶቹ ሲደማመር፣ ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ራሱን ችሎ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለማስመጣት፣ የሚወስደው ብድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም፤ አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያገኝ ድርጅት ስለሆነ፣ ብዙም አሳሳቢ እንዳልሆነ ይገልፃሉ - አይኤምኤፍና የአለም ባንክ።
ካሁን በፊት ያልነበረና አምና የተጀመረ ሌላ የብድር አይነትም አለ - “የውጭ የቦንድ ብድር”። መንግስት፣ በአስር አመት ብድር እንደሚመልስ ቃል በመግባት (ቦንድ በመሸጥ/ ማለትም ምስክር ወረቀት በማስያዝ)፣ አምና አንድ ቢሊዮን ዶላር ተበድሯል። እንዲህ አይነቱ ብድር፣ “ለዚህኛው” ወይም “ለዚያኛው” ፕሮጀክት ተብሎ የሚመጣ ስላልሆነ፣ ለመንግስት አመቺ ነው። ነገር ግን፣ ወለዱ ከፍተኛ ነው - ከሌሎች ብድሮች ጋር ሲነፃፀር፣ የዚህኛው ወለድ ከሦስት እጥፍ በላይ ነው። የአብዛኞቹ ብድሮች ወለድ፣ በአመት ከ2 በመቶ በታች ነው። የቦንድ ብድሩ ወለድ ግን፣ 6.6 በመቶ።
መንግስት፣ ዘንድሮ 1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ብድር ለመጨመር፣ ድርድር እንደጀመረ ተገልጿል።
ይህንን ነው፣ “በጣም አሳሳቢ” ብለው የሚፈርጁት - የአለም ባንክና አይኤምኤፍ። አንደኛ ነገር፣ ከጥቂት ዓመታት ውስጥ፣ የውጭ እዳው በፍጥነት እየተገዘፈ መምጣቱ አሳሳቢ እንደሆነ ይገልፃሉ። ሁለተኛ ነገር፣ የብድሩ ዓይነት፣ ለከፍተኛ የወለድ ክፍያ የሚዳርግ መሆኑ ደግሞ፣ ተጨማሪ ስጋት እንደሆነ ይጠቅሳሉ።
ከ2002 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር፣ መንግስት ለእዳ ክፍያ የሚያውለው የውጭ ምንዛሬ፣ ከ111 ሚ.ዶ ወደ 970 ሚ.ዶ ከፍ ብሏል። ከዚሁ ውስጥ፣ የወለዱ መጠን ስንት እንደሆነም ይታወቃል። በ2002 ዓ.ም፣ የወለዱ መጠን 42 ሚ.ዶ ነበር። አምና ደግሞ፣ የወለድ ክፍያው 250 ሚ.ዶ።
የእዳ ክፍያ ከነወለዱ፣ ባለፉት አምስት አመታት፣ ወደ ስምንት እጥፍ ጨምሯል። ይህንን የሚያካክስ፣ የኤክስፖርት ገቢ እየጨመረ ይመጣል ተብሎ ነበር የታሰበው። ነገር ግን፣ ባለፈት አራት ዓመታት፣ ከኤክስፖርት የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ አላደገም። 3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ላይ ቆሟል። የእዳ ክፍያን ከነወለዱ ለመሸፈን የሚያስችል የኤክስፖርት እድገት አለመገኘቱ፣ ትልቁ አሳሳቢ የኢኮኖሚ ችግር ነው። እንዲያውም፣ ፈታኝ ቀውስ ያልተፈጠረው በሁለት ምክንያቶች ነው። አንደኛ፣ በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ፣ መንግስት፣ በነዳጅ ግዢ ሳቢያ ብዙ የውጭ ምንዛሬ ከማፍሰስ ድኗል። ሁለተኛ፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በየአመቱ የሚልኩት የውጭ ምንዛሬ ጨምሯል።
የውጭ ብድር እንዳለፉት አምስት ዓመታት በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ግን፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እየጎላ መምጣቱ አይቀርም።
በሌላ በኩል፣ እንደውጭ ብድር፣ የመንግስት የአገር ውስጥ ብድርም እየጨመረ እንደመጣ፣ የገንዘብ ሚኔስቴር ሪፖርት ይገልፃል። በ2003 ዓ.ም፣ የብድር ክምችቱ ከ120 ቢሊዮን ብር በታች ነበር። አምና ወደ 300 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ደርሷል።

Monday, 31 August 2015

Who Owns the Nile ?

ይ ይ ር  ም  ል !! 66% ለግብፅ - 22% ለሱዳን  ቀሪው 12% በ ኢቫፖሬሽን ይሚጠፋ !!! ኢትዮጽያ 0% !! #Abiy1702     Who owns the Nile ? Abiy1702

Who owns the Nile? It's more complicated than you think
Source: Al Jazeera and agencies

Tuesday, 4 August 2015

ወዳጅና ጠላት ያለየበት ጦርነት !!

ወዳጅና ጠላት ያለየበት ጦርነት

ምዕራባዉያን መንግሥታት ISISን በምድር የሚወጉትን የኢራቅና የሶሪያ ኩርዶችን በቀጥታ፤የቱርክ ኩርዶችን ደግሞ በተዘዋዋሪ ያስታጥቃሉ።ቱርክ ኩርዶችን ትወጋለች፤ ኩርዶችም ቱርክን።ምዕራባዉን መንግሥታት፤ቱርክና አረቦች የደማስቆ ገዢዎችን የሚወጉ አማፂያንን ይደግፋሉ።ISISም የደማስቆ ገዢዎችን ይወጋል።

ወዳጅና ጠላት ያለየበት ጦርነት

የዋሽግተን፤ ብራስልስ ጥብቅ ወዳጆ፤የሪያድ፤ ዶሐ፤አማን፤ ኤርቤል ታማኞቻቸዉን አስቀድመዉ የቴሕራን-ደማስቆ ጠላቶቻቸዉን እየወጉ፤እያስወጉ፤ ደሞ በተቃራኒዉ ከቴሕራን፤ ደማስቆ፤ ጠላቶቻቸዉና ጋር እንደ ወዳጅ ባንድ አብረዉ ISISን ይዋጋሉ።ተቃራኒዎችን እንደ ጠላት እያዋጋ፤ እንደ ወዳጅ ባሳበረዉ ጦርነት አልተካፈለችም እንዳትባል ተዋጊዎችን እየረዳች፤ ተካፍላለች እንዳይባል ጦር አላዘምትም እያለች ስታቅማማ የነበረች አንድ ያካባቢዉ ሐገር ነበረች።ቱርክ።ባለፈዉ ሳምንት ግራ-አጋቢ አቋሟን ቀይራ፤ከግራ አጋቢዉ ጦርነት በሁለት ተቃራኒ ግንባር ተሞጀረች።
የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆርጅ ዳብሊዉ ቡሽ እንደ ፊት አዉራሪ፤ የያኔዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር እንደ አጋፋሪ ኢራቅን ሲወርሩ አንድ የቱርክ ፖለቲከኛ ጠይቀዉ ነበር።« ሳዳም ሁሴን በርግጥ ከሥልጣን ይወገዳሉ፤ ግን አዲሱ ለዉሬንስ ማን ይሆን?» ብለዉ።
ጀላቢያ፤ ጥምጣም፤ ቁድራቸዉን ለብሰዉ፤ ሴሞ (ጎራዴያቸዉን) ታጥቀዉ አረብኛዉን ሲንያቆረቁሩት-አረብ፤ ሱፍ-ከራባት ለብሰዉ-በእንግሊዝኛ ነገር ሲቆላልፉ-ዲፕሎማት፤ ሸሚዝ፤ ቁምጣቸዉን አጥልቀዉ መሬት ሲቆፍሩ-የሥነ-ዕብን ተመራማዊ (አርኪዎሎጂስት)፤የጦር መለዮ፤ ማዕረጋቸዉን ሲያጠልቁ-ሻምበል ይመስሉ ነበር።ቶማስ ኤድዋርድ ለዉሬንስ።ወይም ለዉሬንስ-ዘ-አረቢያ። ሁሉንም ነበሩ።ከሁሉም በላይ ብሪታንያዉ።
ታላቅዋ ብሪታንያ መካከለኛዉ ምሥራቅን በተለይም ዛሬ እስራኤል፤ ፍልስጤም፤ ዮርዳኖስ፤ ሶሪያ፤ ሳዑዲ አረቢያ፤ ኢራቅ ተብለዉ የሚጠሩትን ሐገራት ከቱርክ እጅ ፈልቅቃ ለመዉሰድ ለነበራትን የረጅም ጊዜ ዕቅድ ገቢራዊነት አረቦችን ከጎኗ ያሰለፉ ብልጣ-ብልጥ ሰላይ፤ በሳል ዲፕሎማት፤ የጦር መኮንን ነበሩ።
በመጀመሪያዉ የዓለም ጦርነት ወቅት በለዉሬንስ አግባቢነት ከብሪታንያ ቅኝ ገዢ ጦር ጋር የዘመተዉ የአረብና የኩርዶች ጦር የቱርክን ጦር በየሥፍራዉ ሲገዘግዝ ቆይቶ ጥቅምት 1918 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ደማስቆን ሲቆጣጠር የአረብ-ቱርኮች ጠብ ከረረ።አረቦች ለአዲስ ገዢዎቻቸዉ አደሩ። የዚያኑ ያክል የፍልስጤም እና የኩርድ ሕዝብ የነፃነት ሕልም ቢያንስ እስከ ዛሬ እንደበነነ ቀረ።
አረቦችን ከቱርክ ቀምቶ ለብሪታንያ በብሪታንያ በኩል ለዩናይትድ ስቴትስ ያስረከበዉ ጦርነት ባበቃ በ85ኛ ዓመቱ-በ2003 የቱርኩ ፖለቲከኛ እንደዘበት የወረወሩት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ በርግጥ የለዉም።መልዕክቱ ግን ኢራቅን ከኢራቃዊዉ ገዢ ቀምቶ ለዋሽግተኖች ለማስረከብ፤ አረብን ሐይማኖት፤ ባሕል፤ ከሚጋሩት ቱርኮች ቀምቶ ለብሪታንያዎች፤ በብሪታንያ በኩል ለአሜሪካኖች ያስረከበዉን አይነት ሴራን-የሚያቀነባብረዉ ማነዉ ነዉ-ነበር።ላሁኑ አላወቀንም።
የዋሽግተንና የለንደን መሪዎች በ2003 ኢራቅ ላይ የለኮሱት ጦርነት ግን እስከያኔ-አረብን ከኩርድ፤ ሱኒን ከሺዓ፤ ክርስቲያንን-ከያዚዲ ቀይጣ ታኖር የነበረችዉን ሐብታም፤ ሥልታዊት፤ታሪካዊት ሐገርን የአሸባሪዎች መፈልፈያ፤ የሽብር ቋት፤ የእልቂት አብነት እንዳደረጋት መቀጠሉ ግልፅ-እርግጥም ነዉ።የኢራቅ መጥፋት፤ አንድነቷ መሸራረፍ፤ ሕዝቧ ማለቅ የጀመረበት ስምንተኛ ዓመት ሲዘከር ሶሪያ ላይ የተቀጣጠለዉ የእልቂት ቋያ የመካከለኛዉ ምሥራቅን የታሪክ ጎተራ፤ የዕዉቀት፤ ሥልጣኔ ምድር፤ የአረብ ብሔረተኞችን ማዕከል ከትቢያ እየቀየጣት ነዉ።
ከአምና ጀምሮ ዓለም አቀፍ አሸባሪነቱ ዕለት በዕለት የሚዘገብበት የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS በምሕፃሩ) የፕሬዝደንት በሽር አልአሰድን መንግሥት ያስወግዳል በሚል እምነት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ፤ በማወቅ ይሁን ባለማወቅ ከሪያድ ዶሐዎች ገንዘብ፤ ከቱርኮች መሰልጠኛ ምድር፤ ከምዕራባዉያን ዲፕሎማሲና የጦር ሜዳ ቁሳቁስ ያገኛል ይባል ይባል ነበር።
ቡድኑ የ«ረዳቶቹን» ዜጎችና ወዳጆች «መንደፍ» ሲጀምር ግን በይድረስ ይድረስ የተደራጀዉ ተዘዋዋሪ ትብብር በተቃራኒ ጎዳና ይሾር ያዘ።
ዩናይድ ስቴትስ ዓለምን አስተባብራ አሸባሪዉን ቡድን በጄት መደብደብ ከጀመረችበት አምና ጀምሮ-ቱርክ እንደ አብዛኛዉ ዓለም በተለይም እንደ ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባልነቷ ድጋፍዋን አልነፈገችም።ድጋፏ ግን የአንካራ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ አጥኚ ሁሴይን ባግቺ እንደሚሉት በማለዘብ መርሕ ላይ የተመሠረተ ነበር።
«መንግሥት (የቱርክ)ISISን እንደሚዋጋ አስታዉቋል።ይሕ በምዕራባዉያንና በኔቶ ዘንድ ላለፈዉ ዓንድ ዓመት በግልፅ የሚታወቅ የቱርክ መንግሥት መርሕ ነዉ።ይሁንና በተጨባጭ ቱርክ ባለፉት ሁለት ዓመታት የምትከለዉ የማለዘብ መርሕ ነበር።ምክንያቱም ISIS 49 የቱርክ ዲፕሎማቶችን ከአንድ መቶ ቀናት በላይ አግቶ ነበር።በዚሕም ምክንያት ቱርክ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ነበረች።ይሁንና ዲፕሎማቶቹ ከተለቀቁ በሕዋላ የቱርክ ፀረ- ISIS አቋም በጣም ተጠናክሯል።»
የአንካራ መሪዎች ISISን በመዉጋትና ባለመዉጋት መሐል ቢቃረጡም የደማስቆ ገዢዎችን ለማስወገድ የሚደረገዉን ዉጊያ ከመደገፍ ግን አልቦዘኑም።የረጅም ጊዜ ጠላታቸዉን የኩርድ ሰራተኞች ፓርቲ (PKK) ሲሆን በድርድር፤ ካልሆነም በሐይል፤ የነፍጥ ዉጊያዉን ለማስቆም መጣራቸዉንም አላቋረጡም ነበር።
በቅርቡ ቱርክ በተደረገዉ ምርጫ PKKን ይደግፋል ተብሎ የሚታማዉ የቱርክ ኩርዶች ፓርቲ ያልተጠበቀ ድጋፍ ማግኘቱ፤ ምዕራባዉያን ለኢራቅና ለሶሪያ ኩርዶች በሚሰጡት ሁለንተናዊ ድጋፍ ላይ ሲታከል የኩርድ ነፃነት አቀንቃኞችን የሚያነቃ-ነዉ የሆነዉ።
የቱርክ መንግሥትና ከ1980ዎቹ ጀምሮ በደማስቆና በባግዳድ ገዢዎች እየተረዳ ቱርክን የሚወጋዉ PKK ለሰወስት ዓመታት ያደረጉትን ድርድር በምርጫዉ ማግስት ሲያፈርሱ ከኢራቅ ኩርዶች የተሰማዉ የአንካራን መሪዎች አያሰጋም ማለት አይቻልም።
ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በምዕራባዉያን መንግሥታት ድጋፍ ሰሜን ኢራቅ ኬርቤላ ላይ መንግሥት አከል-አስተዳደር የመሠረቱት የመስዑድ ባርዛኒ ማስጠንቀቂያ «ጌታዋን የተማመነች----» የሚያሰኝ፤ ከጠንካራ ሐገር መሪ ያልተናነሰ ነበር።«ቱርክ የሠላም ስምምነት ሐሳብ አቅርባ PKK ሐሳቡን ዉድቅ ካደረገዉ PKKን ለመቃወም ዝግጁ ነን።ቱርክ PKKን ለማጥፋት በሚል በኛ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች ግን እራሳችንን ለመከላከል ዝግጁዎች ነን»
በዚሕ መሐል ነበር የISIS አባል እንደሆነ የታመነ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቱርክን ከሶሪያ ጋር በሚያዋስነዉ የድንበር ከተማ 32 የቱርክ ዜጎችን አጥፍቶ የጠፋዉ።ዛሬ ሁለት ሳምንቱ።እርምጃዉ አንካራ ከጦርነቱ እንድትገባ፤ ዘላቂ ስልቷንም እንድታጤን፤ ለምዕራባዉያን ግፊት እጇን እድትሰጥም ጥሩ ምክንያት ነዉ የሆነዉ።
ይሁንና የአንካራ መሪዎች ለዘላቂ ጥቅማቸዉ የሚበጀዉን ሳያሰሉ ተንደርድረዉ ከጦርነቱ አልተሞጀሩም።የቱርክ ባለሥልጣናት PKKን ለመቅጣት የሐይል እርምጃ ቢወስዱ ምዕራባዉያን ወዳጆቻቸዉ «እንዳይንጫጩ» በተለይ ከዋሽግተን መተማመኛ መያዝ ነበረባቸዉ።
አንካራዎች የሁለት ግንባር ዘመቻ ለማወጅ እንዲመቻቸዉ የPKK ሸማቂዎችም ሳይተባበሯቸዉ አልቀረም-ቢያንስ በተዘዋዋሪ።የቡድኑ ታጣቂዎች አፈነዱት በተባለ ቦምብ ሰወስት የቱርክ ወታደሮች ተገደሉ።የግድያዉ ለቱርኩ ፕሬዝደንት ለሬሴፕ ጠይብ ኤርዶኻን «ሳይደግስ አይጣላም» አይነት ነበር።«ብሔራዊ ፀጥታችንንና ወንድማዊ አንድነታችንን ከሚያጠቁ ሐይላት ጋር የሠላም ድርድር መቀጠል አይቻልም።»
ወትሮም የፈረሰዉ ድርድር ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ።ጦርነቱ ቀጠለ።የቱርክ የጦር ጄቶች ኩርዶችን ለመምታት ወደ ሰሜን ኢራቅ፤ ISISን ለመዉጋት ወደ ሶሪያ ይከንፉ ያዙ።የቱርክ መንግሥት በቱርኮች ላይ የከፈተዉን ጥቃት አቁሞ ድርድሩን እንዲቀጥል ጀርመንና አንዳድ የአዉሮጳ መንግሥታት መጠየቃቸዉ አልቀረም።ዩናይትድ ስቴትስ ግን የቱርክን እርምጃ ደግፋለች።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሐገራት ዲፕሎማቶችም ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ ባደረጉት ስብሰባ የቱርክን እርምጃ ደግፈዋል።ዋና ፀሐፊ የንስ ሽቶልተንበርግ ከተባባሪያችን ቱርክ ጎን አንቆማለን ነዉ-ያሉት።ያዉም በፅናት።
«ቱርክ ደጃፍ ላይ እና ኔቶ ድንበር አጠገብ ሥላለዉ አለመረጋጋት ለመነጋገር ዛሬ መሰብሰባችን ተገቢ ነዉ።ኔቶ ሁኔታዉን በቅርብ እየተከታተለ ነዉ።ከአባላችን ቱርክ ጎን በፅናት እንቆማለን።»
PKK ጀርመንን ለመሳሰሉ ሐገራት አሸባሪ ድርጅት ነዉ።ጀርመንን ጨምሮ ምዕራባዉያን መንግሥታት ISISን በምድር የሚወጉትን የኢራቅና የሶሪያ ኩርዶችን በቀጥታ፤የቱርክ ኩርዶችን ደግሞ በተዘዋዋሪ ያስታጥቃሉ።ቱርክ ኩርዶችን ትወጋለች፤ ኩርዶችም ቱርክን።ምዕራባዉን መንግሥታት፤ቱርክና አረቦች የደማስቆ ገዢዎችን የሚወጉ አማፂያንን ይደግፋሉ።ISISም የደማስቆ ገዢዎችን ይወጋል።ሁሉም ፀረ-ደማስቆ ናቸዉ።
የባግዳድ ገዢዎች የሳዳም ሁሴንን ቤተ-መንግሥት የተረከቡት ከዋሽግተኖች ነዉ።ዋሽግተን የቴሕራን ጠላት ናት።የባግዳድ ገዢዎች የቴሕራን፤ በቴሕራን በኩል የደማስቆ ወዳጆች ናቸዉ።በዚሕም ሰበብ ባግዳዶች-ደማስቆን አይነኩም።ዋሽግተን፤ ብራስልስ፤ የአረብ ነገስታት፤አንካራ፤-ቴሕራን፤ ደማስቆ፤ባግዳድ፤ ሒዝቦላሕ፤ ኩርዶች ISIS ን ይወጋሉ።ሁሉም የISIS ጠላት ናቸዉ።አንካራ ኩርዶችን ትወጋለች።ዋሽግተን፤ ብራስልስ፤ አረቦች ኩርዶችን ያስታጥቃሉ።የተሳከረ ጦርነት።ግን ሚሊዮኖች ያልቃሉ።ይሰደዳሉ።እስከመቼ-አይታወቅም።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

Saturday, 25 July 2015

ወንጀለኛን (ተጠርጣሪን) የመያዝ አጠቃላይ አካሔድ :: Law

በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ወንጀለኛን (ተጠርጣሪን) የመያዝ አጠቃላይ አካሔድ - Abyssinia law 


በዚህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የወንጅል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር ስለመዋል ወይም ስለመያዝ የሚመለከቱመሠረታዊ ጉዳዮችን ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን የሰዎች የነፃነት መብትና በፖሊስ በወንጀልተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ስለመዋል መካከል ስላለስ ግንኙነት በትንሹ ገለፃ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎችየሚያዙባቸውን መንገዶችና እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ የሚደነግገውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍልበጥልቀት ለመርመር ሙከራ ተደርጓል፡፡
የመያዝና የሕገ መንግሥቱ የነጻነት መብት ግንኙነት
የኢ... ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17 (1) ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ነፃነቱን እንደማያጣ በግልፅይደነግጋል፡፡ ይህም ማለት በንዑስ አንቀጽ (2) እንደተብራራው ማንኛውም ሰው ክስ ሳይቀርብበበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰርእንደማይችል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በሌሎች ሕጎች በግልፅ በተደነገጉ ሁኔታዎች የዜጎች የነፃነት መብት ሊገደብ እንሚችል የሕገመንግሥቱ ‹‹በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ›› የሚለው አገላለፅ ያሳያል፡፡ በመሆኑም  በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ማንኛውም የወንጀል ድርጊት የፈፀመ ሰው ወይም በወንጀል ድርጊት የተጠረጠረ ሰው በፖሊስ የሚያዝበት አግባብ ሊፈጠርእንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡  ይህም ሲሆን ወንጀሉን የፈፀመው ሰው የሕገ መንግሥቱን ዓላማና መንፈስ በጠበቀ መልኩ ነፃነቱመገደቡን መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ በመቀጠል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ እውቅና የተሰጣቸውና በአሁኑ ሰዓትበማገልገል ላይ የሚገኙትን ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶችን እንዲሁም የአያያዝ ሥርዓቶች እንቃኛለን፡፡
በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶች
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ወንጀለኛን በሦስት ዓይነት መንገዶች በቁጥጥር ሥር ማዋል ይቻላል፡፡ እነርሱም የሚከተሉትናቸው፡፡
በፖሊስ መጥሪያ መሠረት ወንጀለኛን መያዝ
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ
ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት ዓይነት ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶች መካከል በፖሊስ መጥሪያ መሠረት የሚደረግ አያያዝ እንደ መርህሲቆጠር የሚቀጥሉት ሁለት መንገዶች በልዩ ሁኔታ የሚተገበሩ (exceptions) ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ በሚከተለው ጽሑፍበወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ለእያንዳንዱ የመያዣ ዘዴዎች የተቀመጡ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡
በፖሊስ መጥሪያ መሠረት ወንጀለኛን /ተጠርጣሪንበቁጥጥር ሥር ስለማዋል
የፖሊስ መጥሪያ ማለት በመርማሪ ፖሊስ ተዘጋጅቶ ወንጀሉን ፈፅሟል ተብሎ ለተጠረጠረው ግለሰብ በፖሊስ ጣቢያ እንዲቀርብበዚሁ መርማሪ ፖሊስ አማካኝነት የሚላክ የመጥሪያ ወረቀት ነው፡፡ ለዚህም አግባብነት ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግቁጥር 25 ነው፡፡ ይህ አንቀጽ እንደሚከተለው ይነበባል፡
አንቀጽ25. የተከሰሰውን ሰው ወይም የተጠረጠረውን ሰው ስለመጥራት
አንድ ሰው የወንጀል ስራ መፈፀሙን ለማመን መርማሪ ፖሊስ ምክንያት ያለው ሆኖ በሚገኝባቸው ሁኔታች ሁሉየተባለው ሰው ቀርቦ እንዲጠየቅ ፖሊሱ እንድትቀርብ በሚል በጽሑፍ  ትዕዛዝ ሊጠራው ይችላል፡፡
ስለዚህ በዚህ ሕግ ቁጥር መሠረት በፖሊስ ፊት እንዲቀርብ መጥሪያ የደረሰው ሰው ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ በአንቀጽ 26 በተሰጠውሥልጣን መሠረት መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው እንዲያዝ አስፈላጊውን ርምጃ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን በሕጉ በአንቀጽ 25 መሠረትየመጥሪያ ወረቀት ለመስጠትና የጥሪ ወረቀት ደርሶት በፖሊስ ፊት መቅረብ ያልቻለን ሰው ለመያዝ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎችሊሟሉ የግድ ይላል፡፡
የመርማሪው ፖሊስ በቂ ምክንያት ያለው መሆኑ
ይህም ማለት መርማሪው ፖሊስ መጥሪያ ሊልክለት የተዘጋጀው ሰው ወንጀሉን ፈፅሞታል ብሎ እንዲያምን የሚያስችለው ምክንያትሊኖረው ይገባል፡፡ በሌላ አገላለፅ መርማሪ ፖሊስ ያለምንም በቂ ምክንያት የመጥሪያ ወረቀት በማዘጋጀት መላክ አይችልም፡፡በዋነኛነት የዚህ ቅድመ ሁኔታ አላማ የመርማሪ ፖሊሱን ሥልጣን ገደብ ለማበጀት  ታስቦ የተቀረጸ ይመስላል፡፡ ስለዚህ መርማሪውፖሊስ  መጥሪያ የሚላክለት ሰው ወንጀሉን ፈፅሟል ብሎ እንዲያምን ያደረገውን ምክንያት በዝርዝር እንዲገልፅ ሕጉ ያስገድዳል፡፡
የመርማሪው ፖሊስ ሥልጣን ብቻ ስለመሆኑ
ከዚሁ የሕግ አንቀጽ በቀላሉ እንደምንረዳው ተጠርጣሪውን እንዲቀርብ የማዘዝ ወይም ሳይቀርብ ሲቀር የመያዝ ሥልጣን የተሰጠውለመርማሪ ፖሊስ ብቻ ነው፡፡ ይህንንም ‹‹መርማሪው ፖሊስ›› ተብሎ ከተገለፀው የአንቀጽ 25 ክፍል መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላአገላለፅ ከመርማሪው ፖሊስ ውጭ ያሉ ግለሰቦች ተጠርጣሪውን የመጥራት ወይም የመያዝ ሥልጣን የሌላቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡
የመጥሪያ ትዕዝዙ በጽሑፍ የቀረበ መሆን
ከላይ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ መርማሪ ፖሊሱ የመጥሪያ ትዕዛዙን ሕጉ በሚያዘው መልኩ ማለትም በጽሑፍያዘጋጀ መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለበት፡፡ ከጽሑፍ ውጭ ያሉ የመጥሪያ መንገዶች ለምሳሌ፡-የቃል መጥሪያ በሕጉ ያልተፈቀደበመሆኑ መርማሪው ፖሊስ ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትና የተብራሩት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላትሲችሉ በፖሊስ መጥሪያ መሠረት ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር የማዋል ዘዴ ተግባራዊ መሆን ይችላል፡፡
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለመያዝ
የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ማለት ፖሊስ ተጠርጣሪን እንዲይዝ ያስችለው ዘንድ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የሚሰጥ ሰነድ ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 54 መሠረት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚከተሉትሁለት መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ ያስፈልጋል፡፡
ወንጀለኛውን /ተጠርጣሪውንወደ ፍርድ ቤት ለማቅረብ በሌላ መንገድ የማይቻል መሆኑ
በዚህም መሠረት መርማሪው ፖሊስ ለጥያቄ የፈለገውን ሰው አቅርቦ ለመጠየቅ በማናቸውም መልኩ ያልቻለ እንደሆነ የፍርድ ቤትየመያዣ ትዕዛዝ መጠየቅ ይችላል፡፡ መርማሪው ፖሊስ ተጠርጣሪውን ሊይዝ የሚችልባቸው አመቺና ህጋዊ መንገዶች ካሉ ፍርድ ቤቱየመያዣ ትዕዛዝ መስጠጥ አይኖርበትም፡፡ ለምሳሌ፡በአንቀጽ 25 መሠረት የመጥሪያ ወረቀት ለተጠርጣሪው በመጀመሪያ ደረጃመላክ ሲችል ይህን ሳያደርግ ቀርቶ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ መጠየቅ አይችልም፡፡
ወንጀለኛው በፍርድ ቤት መቅረቡ ፍፁም አስፈላጊ ሲሆን
ፍርድ ቤቱ የመያዣ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፊት የሰውየው በፍርድ ቤት ወይም በፖሊስ ፊት መቅረብ ፍፁም አስፈላጊ መሆኑንማጣራት ይኖርበታል፡፡ ተጠርጣሪው በፖሊስ ፊት በቅረቡ በብዙ ምክንያቶች የተነሳ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ከነዚህም መካከል፡-ቃልን ለመቀበል፣ ለአካል ምርመራ፣ ለአሻራ ምርመራ፣ ማስረጃዎችን እንዳያጠፋ ለማገድ ወይም ምስክሮች ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድርለማድረግ ተጠርጣሪውን በፖሊስ ወይ በፍርድ ቤት ማቅረብ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜወንጀለኛውን በፍርድ ቤት ማቅረብ  አስፈላጊ የማይሆንባቸው ጊዜዎች አሉ፡፡
ለምሳሌ፡ጉዳዩ ተከሳሹ በሌለበት (trial in abstentia) በፍርድ ቤት መታየት የሚችል ከሆነ የማያዣ ትዕዛዝ የማይሰጥበት አግባብይኖራል፡፡ ሲጠቃለል ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች መሟላት መርማሪ ፖሊሱ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንዲያገኝናወንጀለኛውን እንዲይዝ ያስችሉታል፡፡
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለመያዝ
የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች፡የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 21(2) አንዳንድ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ሲፈፀሙ ፖሊሱወንጀለኛውን የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ሳያስፈልገው ሊይዘው እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ወንጀሉ የእጅ ከፍንጅ ከመሆኑበተጨማሪ አንቀጽ 21 (2) እና 50 እንደየቅደም ተከተላቸው የሚከተሉትን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀምጣሉ፡፡
ወንጀሉ የክስ አቤቱታ መቅረብ የማያስፈልገው መሆን
የእጅ ከፍንጅ ወንጀሉ ወር በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ መሆን ናቸው፡፡
በዚህም መሠረት ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ሲችሉ በአንቀጽ 50 መሠረት ማንኛውም ሰው ወይም የፖሊስሰራዊት ባልደረባ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲፈፅም የተገኘውን ግለሰብ መያዝ ይችላሉ፡፡
የእጅ ከፍንጅ ያልሆኑ ወንጀሎች፡የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 51(1) ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀልአድራጊውን የሚያዝበት ሁኔታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ ይህም ማለት ወንጀል አድራጊው ወንጀሉን ሲፈፅም በአካል ያልተያዘቢሆንም እንኳን ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀለኛውን የሚይዝባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ አንቀጽከዘረዘሩት ሁኔታዎች መካከል እጅግ አወዛጋቢና ውይይት የሚያስፈልገው ጉዳይ ቢኖር  በንኡስ አንቀጽ 1 (ሥር ተፅፎ የምናገኘውድንጋጌ ነው፡፡ ይህም ቃል በቃል እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
 አንቀጽ 51 (1)
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ መያዝ የሚችለው፡-
ከአንድ አመት በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ለመስራት ዝግጁ የሆነውን ወይም ሰርቷል ተብሎ በሚገባ የተጠረጠረውንሰው፡
በዚህ አንቀጽ መሠረት ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀለኛን ለመያዝ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ፖሊሱ የሚይዘው ሰው ወንጀሉን መፈፀሙን በሚገባ የጠረጠረው መሆን
ወንጀሉ ከአንድ አመት በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ መሆን ናቸው፡፡
ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደምንችለው የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ ወንጀለኛውን /ተጠርጣሪውንለመያዝ የሚያስችል እጅግየተለጠጠ ሥልጣን መጎናፀፋቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም 1997 . በወጣው የኢ... የወንጀል ሕግ መሠረት አብዛኛዎቹየወንጀል ዝርዝሮች አንድ አመትና ከዚያ በላይ የሚያስቀጡ በመሆናቸው ይህ አንቀጽ የፖሊስ ባልደረባዎች በብዙ ወንጀሎችያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎችን እንዲይዙ ሊያደርግ ያስችላል ይህ ደግሞ የፖሊስ ባልደረባዎች ስልጣናቸውን በአግባቡናበሕጉ መሠረት እንዳያከናውኑ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
የአያያዙ ሁኔታ
በዚህ ክፍል ፖሊስ ወንጀለኛውን ለመያዝ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ምን ምን ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለበት እንመለከታለን፡፡የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 56 እንደሚያስቀምጠው የመጀመሪያው የፖሊስ ስራ የሚሆነው ለመያዝ የተዘጋጀውንሰው ማንነት በደንብ ለይቶ ማወቅ (ማጣራትይኖርበታል፡፡ ከዚህ በመቀጠል የፍርድ ቤት የመያዝ ትዕዛዝ የተሰጠው እንደሆነይህንኑ ትዕዛዝ ለሚይዘው ሰው ማንበብ ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ይህን የፍርድ ቤት የመያዝ ትዕዛዝ የሚይዘው ሰው የጠየቀውእንደሆነ ማሳየት እንዳለበት ከሕጉ መረዳት እንችላለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች መሟላት ሲችሉ የሚያዘው ሰው  በቃል ወይም እጁን በመስጠት እንዲያዝ ፈቃደኝነቱን ካላሳየ ፖሊሱሰውየውን በመንካት ወይም በመጨበጥ ለመያዝ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚያዘው ሰው አልያዝም ብሎ በሃይል የተከላከለ ወይምለማምለጥ የሞከረ እንደሆነ ሁኔታው በሚፈቅደው ተመዛዛኝ ዘዴ ፖሊሱ ሰውየውን ለመያዝ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄፖሊሱ ሊወስደው የሚችለው ››ተመዛዛኝ ዘዴ›› ምን ያክል ነው?  የሚለው ነው፡፡ ይህም ጥያቄ  መልስ ሊያገኝ የሚችለው ተጠርጣሪየሚያሳየውን ባህሪ ወይም ምላሽ ግምት ውስጥ በማስገባት ስለሚሆን ይህ ነው ብሎ እርግጠኛ የሆነ መልስ መስጠት አይቻልም፡፡