
የዛሬ 26ዓመት ኖቬምበር 9 ቀን 1989ዓ/ም የበርሊን ግምብ ፈረሰ!
60 ሚሊዮን ያህል ሰዎች እንዳለቁበት የሚገመተው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲጠናቀቅ ጀርመን ለሁለት ተከፈለች። ማዕከላዊ በርሊንን አልፎ ወደ ምዕራብ ግዛት ለመግፋት የሞከረው የሶቬት ህብረት ሰራዊት የምዕራቡን ክፍል ከተቆጣጠረው የአሜሪካ ጦር ‘ወዴት ነው?’ የሚል ጥያቄ ቀረበለት። ‘ወዴትስ ብንሆን?!’ ብሎ አምልጠው ለአሜሪካ ጦር እጅ የሰጡትን የናዚ ወታደሮች ለመበቀል ያሰፈሰፈው የሶቬት ህብረት ሰራዊት ማዕከላዊ በርሊንን ለቆ ወደ ኋላ እንዲሄድ ተጠየቀ። ሶቬቶች እምቢ ብለው ከአሜሪካ ጋር ጦርነት ውስጥ ሊገቡ ታንኮቻቸውን በማዕከላዊ በርሊን ዝግጁ ማድረግ ሲጀምሩ የሶቬት ህብረት ሊቀመንበር ጆሴፍ ስታሊን ሶቬቶች ወደ ምስራቅ በርሊን እንዲመለሱ እና ወደ ምዕራብ በርሊን የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ እንዲዘጉ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። ይህም በጦርነቱ የተጎሳቆለውን በምዕራብ በርሊን በኩል ያለውን ህዝብ የምግብ አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥበት አደረገ። የምዕራብ በርሊን ህዝብ በርሃብ እና በሞት መሃል ባለበት ሰዓት በአሜሪካዊው ጀነራል ሉዊስ ክሌይ ትዕዛዝ ኦፕሬሽን ቪትልስ ተጀመረ። ኦፕሬሽን ቪትልስ የአሜሪካ አውሮፕላኖች በየቀኑ የምግብ፣ቅቤ፣ለውዝ፣ስጋ፣
ነሃሴ 13 ቀን 1961ዓ/ም በስምራቅ በርሊን በኩል ሶቬት ህብረት የበርሊን ግምብን መስራት እንደጀመረች 50ሽ ያህል የምስራቅ በርሊን ሰራተኞች በምዕራብ በርሊን ካላቸው የስራ ገበታቸው ላይ መሄድ እንዳይችሉ ተደረገ። ይህ ግምብ ወደ ምዕራብ ጀርመን የሚሄዱ የምስራቅ ጀርመንን ሰዎች ለማገድ የተሰራ ሲሆን ለ28ዓመታት ያህል ቆሟል። የዛሬ 26ዓመት ኖቬምበር/ህዳር 4 ቀን 1989ዓ/ም ምስራቅ በርሊን ዓይታው የማታውቀው ዓይነት የህዝብ አመጽ አስተናገደች። እዚህም እዚያም በሚነሱ የነጻነት ጥያቄዎች እርስ በርስ መስማማት ያልቻሉት የምስራቅ ጀርመን መሪዎች ስብሰባ ተቀምጠው እንዴት እና በምን መልኩ ለህዝቡ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው መምከር ይዘዋል። ይሄው ምክክር እስካሁን የት እንደደረሰ እና በቀጠይ ቀናት ስለምን እንደሚመክር ለመግለጽ የምስራቅ ጀርመን ሶሻሊስት ዩኒቲ ፓርቲ ፖሊት ቢሮ አባል የሆኑት ጉንተር ሻቦውስኪ ከምሳቅ እና ምዕራብ በርሊን እንዲሁም ከጣሊያን እና ከስፔይን ከተወጣጡ ጋዜጠኞች ፊት ተቀምጠዋል። በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈውን የጉንተር ሻቦውስኪ ገለጻ ህዝቡ ለማዳመጥ በቴሌቪዥን ስር አፍጥጧ። ኖቬምበር 9 ቀን 1989ዓ/ም!
ሪካርዶ ኤህርማን የሚባል ለጣሊያን ዜና አገልግሎት የሚሰራ ጋዜጠኛ ባለስልጣኑን “የምስራቅ ጀርመን ህዝብ የመጓዝ እና ወደ ሌሎች ሃገራት የመንቀሳቀስ ነጻነቱን ለማክበር የወሰናችሁት ነገር አለ ወይ?” በማለት ጠየቀ።በቃላቸው ቀጥተኛ ምላሽ መስጠት ያልቻሉት ባለስልጣኑ ከያዙት ወረቀቶች ውስጥ አንድኛውን ለይተው በማውጣት “የምስራቅ ጀርመን ዜጋ ሁሉ ማንንም ሳያስፈቅ እና የፖሊስን ይሁንታ ሳይጠይቅ ወደ ምዕራብ ጀርመን ሊሄድ ይችላል።”በማለት አነበቡ። ሌላ ጋዜጠኛ ቀጠለና “ከመቼ ጀምሮ?”ብሎ ባለስልጣኑን ጠየቃቸው። ለዚህ የሚሆን መልስ በያዟቸው ወረቀቶች ውስጥ እንደሌለ የተረዱት ባለስልጣኑ “እኔ እንደሚመስለኝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ፤አሁኑኑ!”በማለት ግራ እየተጋቡ ምላሻቸውን ሰጡ። ይህን የባለስልጣኑን ምላሽ ያደመጡት ነጻነትን ፍለጋ ወደ ምዕራብ ጀርመን ለመግባት ለ28ዓመታት ያህል የበርሊንን ግምብ ሲዘሉ እና ለመዝለል ሲሞክሩ የኖሩ የምስራቅ ጀርመን ሰዎች ባለስልጣኑ ንግግሩን እስኪጨርስ ማድመጥ ሳያስፈልጋቸው ዶማ፣መዶሻ፣ እና ሌሎች ግምብ ለማፍረስ የሚረዱ ንገሮችን ይዞ ወደ በርሊን ግምብ ተመሙ። ልክ የዛሬ 26ዓመት በዛሬው ዕለት የባርነት፣የመለያየት፣የው
በዘመነ ደርግ ቡና በጥሬው ካልሰጣችሁን ለኤርትራ የጦር ድጋፍ እንደርጋለን ሲሊ የኖሩት፣ብሄራዊ ባንክን 5ነጥብ 6ሚሊዮን ዶላር ያጭበረብሩት፣ ‘አይፋ’ የተባለውን መኪና በግድ በቡና ካልቀየራችሁን እያሉ እጅ ሲጠመዝዙ የኖሩት፣ ከኢትዮጵያ ቡና ወስደው አየርባየር ለደቡብ ኮሪያ እየሽጡ ከዚያው ለኢትዮጵያ ወታደሮች ልብስ እየሸመቱ የምስራቅ ጀርመን ምርት አስመስለው ሲያታልሉ የኖሩት የምስራቅ ጀርመን ሶሻሊስቶች በመጨረሻው ሰዓት በህዝብ የነጻነት ትግል ተሽነፉ። ከሶቬት ህብረት ቀጥላ ዋናዋ ወዳጃችን የነበረችውን ሃገር እና አይፋ ለሚባለው መኪናቸው ኢትዮጵያዊያን ‘አይፋ ለናት ሃገሩ ተደፋ’ የተባለላትን ምስራቅ ጀርመንን ሶሻሊዝም በአፍጢሟ ደፋት። የበርሊን ግምብ በፈረሰበት ወቅት የሶሻሊስት ስርዓት አራማጅ በነበረችው ምስራቅ ጀርመን ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ የለም ነበር። በአንጻሩ ካፒታሊስቷ ምእራብ ጀርመን በኢኮኖሚ አቅሟ ከአሜሪካ ቀጥላ ከዓለም ሁለተኛ ነበረች። የበርሊን ግምብ ከፈረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ እኤአ ጥቅምት 3ቀን 1990ዓ/
If You want to see the writers Page :- Kidus Mehalu |
No comments:
Post a Comment