Sunday, 12 July 2015

የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት መመስረቻ የመጀመሪያ ቻርተርን ያረቀቀ ታላቅ ሰው፡፡

Ato KETEMA YEFRU. ሰውዬው ገራሚ ነው፡፡ያለተዘመረለት ጀግና (unsung hero) ይባላል በፈረንጅ አፍ፡፡የአፍሪካ ጀግና፡፡ በታህሳስ 12 1929 ነው ይችን ምድር የተቀላቀለው፡፡ምሁር ነበር፡፡ምሁር ስላችሁ እንደአዳንድ የጊዜው ምሁራን ቴሲስ ከጫት ቤት ገዝቶ ዶክተር ምናምን የሆነ ምሁር አይደለም፡፡በቃ አዋቂ፣ የምሩን ምሁር፡፡

በወቅቱ << BBC the master mind behind the first charter of OAU >> ሲል ያሞካሸው አብዛኞቻችን ግን የማናውቀው ምርጥ የአፍሪካ ልጅ፡፡የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት መመስረቻ የመጀመሪያ ቻርተርን ያረቀቀ ታላቅ ሰው፡፡
ስለ ጉዳዩ ሲነሳ እኛ ኩዋሜ ኑኩርማህ እና አጼ ሀይለስላሴን ነው የምናርፈው አይደል፡፡ከነሱ ያላነሰ (እንደውም ባይበልጥ) ስራ የሰራ ግን ደግሞ ያልተዘመረለት ጀግና ነበረልህ፡፡
በወርሀ ግንቦት 1963 ዓ.ም የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚኒስትሮች ሊቀመንበር ተብሎ
በተመረጠበት ጊዜ ለአሁኑ ደርጅት የመእዘን ድንጋይ የሆነውን የቻርተሩን ረቂቅ ለመጻፍ ከሌሊቱ 5 ሰአት አስከ ቀኑ 9 ሰአት ሳይነሳ ቁጭ ብሎ ነበር የጨረሰ፡፡
በወቅቱ በMonrovia and Casablanca ቡድኖች መካከል የነበረውን እና አህጉሪቱን ወደ ከፋ ክፍፍል ሊመራት በነበረው ከፍተኛ ፍጭትና ክፍፍል ለማደራደር በዋነኝነት የመራ ጀግና፡፡በድርድሩም ሁለቱን ጎራዎች ወደ አንድ ያመጣና የአፍሪካ አንድነት ደርጅትን እንዲወለድ ያደረገ ምርጥ የአፍሪካ ልጅ፡፡
ሰውዬው በተጨማሪም የነሀሴ 1963ቱን ስለ ድርጅቱ ጽ/ቤት መቀመጫ ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመወሰን የውጪ ችጉር የተፈታበትን የዳካሩን የውጪ ጉዳያ ሚኒስተሮች ስብሳበን የመራና ያስወሰነ የእኛ ታሪክ የረሳው ምርጥ የአፍሪካ ልጅ፡፡
ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝና ክስ ደርግ ለ8 አመት አስሮት ሲፈታው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) ውስጥ በከፍተኛ የስራ ሀላፊነት ያገለገለ እና በጥር 14 1994 በጣፊያ ካንሰር ህመም ከዚህ አለም በሞት የተለየ ምርጥ የአፍሪካ ልጅ፡፡
አሁን የማወራልህ ሰው የሀገርህ ሰው ነው፣የአፍሪካ ሰው ነው ፣የአለምም ሰው ነው፡፡የሀገር ኩራትም ነው፡፡ስሙ ከተማ ይፍሩ ይባላል፡፡በቀድሞው ሀረርጌ ክ/ሀገር በጋራ ሙለታ ነው የተወለደው፡፡ከ1961 አስከ 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ነበር፡፡
የህብረቱን ምስረታ ሀምሳኛ አመት ስናከብር አሯሩጠን ከጨረስናቸው መንገዶችና ጎዳናዎች አንድን እንኳን በስሙ ያልሰየምንለትና ኢትዮጵያዊ ጀግና፡፡
ወደድክም ጠላህም ለኔ የ50 አመቱ ያልተዘመረለት ምርጥ ጀግና እሱ ነው፡፡
Like · Comment · 

No comments:

Post a Comment